«ኦሮሞ እና አማራን የሚነጣጥሉ አይሳካላቸውም» የኦሮሞ ድርጅቶች
የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት እና አንገብጋቢ የወቅቱ ጉዳዮችን አስመልክቶ ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ የተባበሩት ኦነግ፣ የኦሮሚያ ነፃነት አንድነት ግንባር እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ አምስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ አተኩረዋል።
አነሱም የኦሮሞ ማንነትን ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ሙከራ፣ አዲስ አበባ ጉዳይ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ሚድያዎች፣ በሃገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥን እና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝምን የሚመለከቱ ናቸው።
- የ ኦሮሞ ማንነት
«ከዚህ ጀርባ ፀረ ኦሮሞ አቋም ያለው የተደረጃ የፖለቲካ ቡድን ስለመኖሩ የሚያመለክቱ በርካታ መረጃዎች ተገኝተዋል» ይላል መግለጫው።
«በማንነታችን ላይ የተቃጣውን ድርጊት ከማንኛውም ጊዜ በላይ እናወግዛለን፤ ድርጊቱን የፈፀሙ በህግ እንዲጠየቁ እንጠይቃለን» በማለት ፓርቲዎቹ መግለጫቸው ላይ አትተዋል።
- አዲስ አበባ ን በተመለከተ
ፓርቲዎቹ «እኛ ኦሮሞ ድርጅቶች አዲስ አበባ ሁሌም የኦሮሞ ሕዝብ ናት፤ ይህ ማለት ግን ከኦሮሞ ውጭ መኖር አይችልም ማለት አይደለም» ሲሉ በመግለጫቸው አትተዋል።
«ሆኖም አንዳንድ የፖለቲካ ድርጀቶች ይህን በመካድ ከተማዋን እያሸበሩ መሆናቸውን ታዝበናል፤ አልፎም በኦሮሞ እና አማራ ሕዝብ መካል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። ቢሆንም አይሳካላቸውም፤ የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝቦች ለውጥ ለማምጣት አብረው ታግለዋልና» ይላል መግለጫው።
መላው ሕዝብ የእኒህን ኃይሎች ሴራ ለማክሸፍ አብሮ መቆም አለበትም ሲል መግለጫው ያክላል።
- ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ሚድያዎች
«ስለዚህ ውጭም ሆነ ሃገር ቤት ያላችሁ ሃገር አማሽ ሚድያዎች በህግም በታሪክም ፊት ተጠያቂ መሆናችሁን አውቃችሁ ከድርጊታችሁ ታቀቡ» በማለት መግለጫው አስገንዝቧል።
- በሃገሪቷ እየታየ ያለውን ለውጥና ሽግግር በተመለከተ
«ነገር ግን እንደማይሳካላቸው የተገነዘቡ የፖለቲካ ቡድኖች በሃሰት የብር ኖቶች ዜጎችን በማታለል የሃይማኖትና የብሄር ግጭት በማስነሳት መንግስት የሌለ ለማስመሰል እየተሯሯጡ እንደሆነ ግልጽ ነው።»
«በመሆኑም አሁን ያሉ ተቋማት በህገ መንግሥቱ መሰረት በትክክል እንዲሰሩ ተደርጎ በነጻ፣ ተአማኒና በቂ ፉክክር በተደረገበት ህዝባዊ ምርጫ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገውን ሽግግር ብቻ የምንደግፍ መሆኑን እንገልጻለን» ሲሉ ድርጀቶቹ አቋማቸውን አንፀባርቀዋል።
- በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝምን በተመለከተ
አንዳንድ ሚዲያዎችም ይህንኑ ተግባር ተያይዘውታል። ስለዚህ እኛ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ፈጽሞ የማንቀበለው መሆኑንና በህልውናችን ላይ የተቃጣ አደጋ አድርገን እንደምንመለከተው እንገልጻለን በማለት ድርጀቶቹ መግለጫቸውን አጠናቀዋል።
No comments