Latest

የኢትዮጵያ መንግስትና የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲዊያ ንቅናቄ በአስመራ ተወያዩ

የኢትዮጵያ መንግስትና የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲዊያ ንቅናቄ

(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስትና የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያ ንቅናቄ በአስመራ ከተማ በተለያዩ ጉዳዮች መወያታቸው ተገለፀ።


የኤርትራ መንግስት ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው፥
 

በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አደም መሀመድ የሚመራው የመንግስት ልዑክና በትህዴን ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬ የሚመራ ልዕኩ በዛሬው ዕለት በአስመራ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

ከዚህ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያቀረቡትን የሰላም ጥሪ ተከትሎ፥ 
  • የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ፣  
  • የኦሮሚያ ነጻነትና አንድነት ግንባር፣ 
  • የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር ፣ 
  • የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት 
አመራሮች ልዑካን አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወስ ነው።

No comments