Latest

ከውጭ የተመለሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተቋቋመ

ፖለቲካ ፓርቲዎች

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ከውጭ የተመለሱ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተቋቋመ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት፥ መንግስት በውጭ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ስምምንት መድረሱን አስታውሰው፤ ስምምነቱም ነፍጥ አንግበው የነበሩ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን፣ ከህረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉብትንና ዘላቂ ኑሮ የሚመሩበትን ሂደት ይጨምራል::

ይህንን በአግባቡ ለምፈጸም በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ውስጥ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈትቤት መቋቋሙንም አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት አቶ ተስፉዬ ይግዙን የፕሮጀክቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን አቶ ፍፁም አስታውቀዋል።

የኢፌዴሪ መንግስት በውጭ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ስምምንት መድረሱን ተከትሎ በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸው ይታወሳል።

ከእነዚህም ውስጥ አርበኞች ግንቦት 7፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ እና ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ተጠቃሽ ናቸው።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በቅርቡ ልኡካቸውን ወደ አዲስ አበባ መላካቸው ይታወሳል።

No comments