የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ በቁጥጥር ስር ዋሉ
(ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር በቁጥጥር ስር የዋሉት በዛሬው እለት አዲስ አበባ አትላስ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው።
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው እለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የአቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወሳል።
ምክር ቤቱ ከአቶ አብዲ በተጨማሪ የ6 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብትም አንስቷል።
ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባላትም፦
- አቶ አብዲ ጀማል ቀሎንቢ – የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግና ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
- ወይዘሮ ራህማ መሀሙድ – የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አብራሂም መሀመድ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ዴቅ አብዱላሂ – የውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
- አቶ ኢብራሂም መሀሙድ ሙባሪክ -የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና
- አቶ ኡመር አብዲ – የኢሶህዴፓ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ናቸው።
No comments