Latest

የቤተ መንግስቱ ክስተት - ሃብታሙ አያሌው



የቤተ መንግስቱ ክስተት

የቤተመንግስት ጠባቂው ኃይል ቀደም ሲል ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሰዎች ቁጥጥር ስር እንደነበረ ይታወቃል።


በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የቤተ መንግስቱ ጠባቂዎች ብቻ ሳይሆኑ የአስተዳደር ሰራተኞችም ሳይቀሩ ሙሉ በሙሉ ተለውጠዋል።



ይህ ለውጥ ገና ሶስት ወራት አልተሻገረም። አዲስ የተቀየሩት የጥበቃ ኃይሎች ዛሬ እረፋዱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው ሲገቡ እገታ በመፈፀም ወደ ሌላ ቢሮ ይወስዷቸዋል።

በዚህ ሁኔታ ግር ግር ተፈጥሮ ከውጭ የመጣው የመከላከያ ኃይል ከበባ ፈፅሞ ሁኔታውን በማክሸፍ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእገታው ተለቀው ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ እንዲገቡ ተደረገ።

በዚህ ሰዓት ዶክተር አብይ እና አቶ ደመቀ በፅህፈት ቤት ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው መግለጫ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ናቸው።

በእጅጉ ትኩረት የሳበው ጉዳይ አፈና የፈፀመው ኃይል ከተመደበ ሦስት ወር ያልሞላውና የደሞዝ ጥያቄ ቢሆን እንኳ ለአስተዳደር የሚቀርብ እንጂ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማገት የመፈፀሙ ጉዳይ ተቀዩባይነት የሌለው መሆኑ ነው።


ለማንኛውም በማያሻማ ሁኔታ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፈፀመበት አፈና ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ከሽፏል። መንግስት ጉዳዩን ህዝብ በሚያረጋጋ መንገድ ለመግለፅ እየተዘጋጀ ነው።

ከፖለቲካ አንፃር ስለ አፈናው ሂደት እና አላማ በግልፅ ይናገራሉ የሚል እምነት ባይኖረኝም መግለጫ ለመስጠት ግን እየተሰናዱ ነው።

No comments