Latest

በግፍ ማሰር ተጠናክሮ ቀጥሏል (ሐብታሙ አያሌው)

በግፍ ማሰር ተጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ህዝብ እንጂ የአንድ ብሔር አይደለችም በሚለው ፅኑ አቋማቸው የሚታወቁ ሁለት የአዲስ አበባ ወጣቶች ታሰሩ።

ቀደም ሲል በርካታ የህወሓት የግፍ እስረኞችን የሽብር ክስ በጠበቃነት ሙያው ያለከፍያ ሲሟገት የነበረው ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ እና በርካታ እስረኞችን ተመላልሶ በመጠየቅ፤ በገንዘብ በመርዳት ሁሌም ከተገፉ ጎን የሚቆመው ሚካኤል መልአከን የዶክተር አብይ መንግስት በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። 


ይህው ዛሬም (ስለ አዲስ አበባ ዝም አንልም፤ በግፍ የታሰሩ ይፈቱ) የሚለውን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ያስተባበሩ አካላት ተለቅመው ታሰሩ።

ትላንት በህወሓት የበላይነት ዘመን ነውጥ ለመምራት አሲረሃል ተብሎ ታስሮ የነበረው የዛሬው የስልጣን ተረኛ የፌደራል አቃቤህግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደና በማህበራዊ ድህረ ገፁ "እናሳያችኋለን" ብሎ በዛተ ማግስት የአዲስ አበባ ወጣት ታፍሶ ወደ ጦላይ በረሃ ተጋዘ።

ታዬ ደንደና ዛሬም በማህበራዊ ድህረገፁ ብቅ ብሎ ተመሳሳይ ዛቻ ፈፀመ፤ ከንቲባው ኢንጅነር ታከለ ኡማ ምንም የታፈሰ ወጣት የለም ብሎ ሲክድ ታዬ ደንዳ በበኩሉ "ፖሊስ ጠረጠርኩ ካለ ማሰር ትላንትም ነበር ዛሬም አለ ነገም ይቀጥላል" የሚል እብሪቱን ፃፋ ከዚያም እስሩ ቀጠለ።

በአዲስ አበባ "የፊንፊኔ ህዳሴ ማህበር " በደማቅ ስነስርዓት እዲመሰረት ሲደረግ አዲስ አበባ የአዲስ አበቤው ናት የሚሉትን እየለቀሙ ማሰር አማራጭ ተደርጓል። የአንዱን የበላይነት በሌላኛው የመተካት ዘመቻው ውጤት በግልፅ እየታየ ነው። የጉድ አገር !!

No comments