Latest

ራያ በሀዘን ድባብ ተከባለች - አምስት ወጣቶች በልዩ ሃይሉ ተገድለዋል

ራያ በሀዘን ድባብ ተከባለች - አምስት ወጣቶች በልዩ ሃይሉ ተገድለዋል

ራያ በሀዘን ድባብ ተከባለች የትግራይ ልዩ ኃይል በመከላኪያ ጥረት ከአካባቢው እየወጣ መሆኑ ከስፍራው በደረሰን መረጃ ማወቅ ተችሏል

  • ከሆስፒታል በደረሰን መረጃ አምስት ወጣቶች በልዩ ሃይሉ ተገድለዋል
  • ሁለት ወጣቶች በሞት አፋፍ ይገኛሉ (Critical)
  • በጥይት የቆሰሉ በርካቶች ሲሆኑ ከተለያየ የከተማዋ አቅጣጫ ወደ ሆስፒታል እና ክሊኒኮች እየገቡ ይገኛል

ይህ በእንዲህ እንዳለ የራያ ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ “ለማንነት መከበር እስከ መስዋዕትነት” በሚል መፈክር በቆራጥነት እየታገለ ይገኛል!!! ከዚህ በሗላ ባርነት በቃን! መታሰር በቃን! መሞት በቃን! መረገጥ በቃን ብሏል!!! ማንነቴን ወይም ሞቴን ብሎ ቆርጦም ተነስቷል። ደግሞም በየትኛውም ጊዜ ህዝብ ያሸንፋል!!!!

መከላከያ ሰራዊቱ ሲገባም “መከላከያ የእኛ” እያለ ህዝቡ የተቀበለው ሲሆን በዚህ ሰዓት አንፃራዊ መረጋጋት ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ ያለው ሰፈር ቢኖርም 01 ቀበሌና ወደ ላይ ያለው ሰፈር ግን አንዳች እንቅስቃሴ የሚባል የለም!!!
ደጀኔ አሰፋ 
አላማጣ በአሁኑ ሰዐት መከላኪያ ድንጋይ በመልቀም መንገድ በመክፈት ህዝቡን በማረጋጋት ላይ ይገኛል አንድ ወጣት ከጥቂት ደቂቃ በፊት በጥይት ተመቶ ወደ ሆስፒታል ገብታል የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው የራያ እናቶች በልጆቻቸው ሞት የመረረ ለቅሶ ላይ ናቸው ፡፡ 

ራያ በሀዘን ድባብ ተከባለች የትግራይ ልዩ ኃይል በመከላኪያ ጥረት ከአካባቢው እየወጣ መሆኑ ከስፍራው በደረሰን መረጃ ማወቅ ተችሏል በትህምክት ያበጠው ህወሓት ፋሽስታዊ ውንብድናው በራያ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ዝም አንልም!! ፍትህ ለራያ ህዝብ!
ስንታየሁ ቸኮል






No comments