Latest

ኦነግ ትጥቁን እንዲፈታ ከመንግስት ለቀረበለት ጥሪ ምላሽ ሰጠ - ትንሳኤ የእርስዎ ራዲዮ



ትንሳኤ የእርስዎ ራዲዮ


በሃዋሳ ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆዬው አስራ አንደኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ሊቀመንበሩን እና ምክትል ሊቀመንበሩን በምወምረጥ ማምሻውን ተጠናቋል።

ለምርጫው ዶክተር አብይ፣ አቶ ደመቀ እና ዶክተር ደብረጽዮን በእጩነት የቀረቡ ሲሆን፤ ከ177 ደምጽ 176 በማግኘት ዶክተር አብይ በሊቀ መንበርነት ሲመረጡ፣ አቶ ደመቀ መኮንን 149 ድምጽ በማግኘት ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል። 


ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ደግሞ 15 ድምጽ አግኝተዋል። ይህ የድምጽ ውጤት: - ሕወሐት እንደ ሌሎቹ እህት ድርጅቶች ለዶክተር አብይ ሙሉ ድምጽ መስጠቷን፣እንዲሁም በትንሹ ከ14 ያላነሱ የሕወሐት አባላት ለአቶ ደመቀ ድምጽ መስጠታቸውን ያመላክታል።

ይህ ሕወሓት ያሳዬው አቋም ከጅምር ለውጡ አኳያ እንደ በጎ የሚታይ ነው።

ጉባኤው በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እና በህግ የበላይነት ላይ ድርድር እንደማይኖር ተስማምቷል። እንዲሁም ሌባ እና ወንጀለኛም ምንም ዐይነት ማንነነት እንደሌለዉ የተሰመረበት ሲሆን፣ በሙስናም ሆነ በሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂነት መረጋገጥ እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሶበታል።
 

ዶክተር አብይ፦“ በበጎዉን እየደመርን መጥፎዉን እየቀነስን ሀገሪቷን እና ህዝቦቿን እናሻግራሀን!”ማለታቸውም ተሰምቷል።
ኦነግ ትጥቁን እንዲፈታ ከመንግስት ለቀረበለት ጥሪ ምላሽ ሰጠ። ኦነግ ጦሩን ትጥቅ አስፈትቶ በአስቸኳይ ወደ ካምፕ እንዲያስገባ መንግስት ጥሪ ቢያቀርም፣ የግንባሩ ቃል አቀባይ “ሕዝባችን -ኦነግ ጦር እንዲፈታ አይፈልግም”የሚል ምላጭሽ ሰጥተዋል። 

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥት የገጠርና ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ ከሁለት ቀናት በፊት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ በአሁኑ ወቅት ሀገር ውስጥ አስታጥቆ እያንቀሳቀሰ ያለውን ጦሩን ትጥቅ እንዲያስፈታ እና ወታደሮቹንም በአስቸኳይ መንግሥት ወዳዘጋጀው ካምፕ እንዲያስገባ መጠየቃቸው ይታወቃል።
 

አቶ አዲሱ “ግንባሩ ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ስምምነት አክብሮ መንቀሳቀስ አለበት” በማለትም ኦነግ ከመንግስት ጋር ለደረሰበት ስምምነት ተገዥ እንዲሆን አሣስበዋል።

የኦነግ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ቶሌራ አደባ ለዚህ የመንግስት ጥሪ በሰጡት ምላሽ፣ ትጥቃቸውን ያልፈቱ የኦነግ ወታደሮች እንዳሉ በማመን፤ “ሕዝባችን ኦነግ ትጥቁን እንዲፈታ ፍላጎት የለውም” ብለዋል። ‹‹በሰሜን፣ በምሥራቅ፣ በመካከለኛውና በደቡባዊ የኦሮሚያ ግዛቶች የታጠቁ የእኛ ወታደሮች አሁንም ድረስ አሉ›› ሲሉም አቶ ቶሌራ አክለው ተናግረዋል፡፡
 

ቃል አቀባዩ ለጀርመን ድምጽ በሰጡት መግለጫ፦" የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት- ኦነግ ትጥቅ እንዳይፈታ ነው” በማለት በይፋ ገልጸዋል። በ11ኛው የኢህ አዴግ ጉባኤ በሊቀመንበርነት የተመረጡት ዶክተር አብይ የመጀመሪያውና ቀዳሚ ሥራቸው ሀገሪቱን ማረጋጋትና የህግ የበላይነትን ማስከበር ሊሆን እንደሚገባ ብዙዎች እያሣሰቡ ባለበት ወቅት ኦነግ ትጥቅ ለመፍታት ፈቃደኛ አለመሆኑ-ከመንግስት ጋር የገባውን ስምምነት እንዳያፈርስበት ብዙዎች ያስጠነቀቃሉ።

ለ150 ሺህ በላይ ላሸቀቡት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቃዮች ሕዝቡ አስቸኳይ እርዳታ እንዲያደርግ ተጠየቀ።
በአውሮፓ ደረጃ የኢትዮጵያውያን ካህናት ማህበር ተመሰረተ የሚሉና ሌሎችንም መረጃዎች አጠናቅረን ይዘን ቀርበናል።

ትንሳኤ-የእርስዎ ራዲዮ!

No comments