Latest

በነገው ዕለት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ስልጣን እንደሚለቁ ተገለፀ!

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ነገ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ።

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመውም፥ ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ ፕሬዚዳንት ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነበር አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስን በመተካት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት።

ሶስተኛው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ነገ ለሚተካቸው አራተኛ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት በምክር ቤቶቹ ፊት ስልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

No comments