Latest

ሰበር ዜና፡ ዶ/ር ዐቢይና አቶ ደመቀ የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ሰበር ዜና፡ ዶ/ር ዐቢይና አቶ ደመቀ የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ሆነው  ተመረጡ

ዛሬ ከሰዓት በኃላ በተካሄደው የግንባሩ የአመራርነት የምርጫ ስነ-ስርዓት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የግንባሩ ሊቀመንበር ሆኖ እንዲቀጥሉ ተመርጠዋል፡፡


አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ ቀጣዩን ድምፅ በማግኘት የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ኢህአዴግን በአመራርነት ለመምራት እጩዎች ሆነው ቀርበው የነበሩት ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከኦዴፓ፣ አቶ ደመቀ መኮንን ከአዴፓ እና ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከህወሓት ናቸው፡፡

ድምፅ በመስጠት 177 ሰው ተሳትፏል፡፡


ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከተሰጠው ድምፅ 176 ድምፅ አግኝተዋል፡፡አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ 149 ድምፅ በማግኘት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ዶክተር ደብረ ፅዮን ገ/ሚካኤል ለምክትል ሊቀመንበርነት ቀርበው 15 ድምፅ አግኝተዋል፡፡


የደኢህዴን ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በምርጫው አለመሳተፋቸው ተመልክቷል፡፡

ምርጫውን የሚመራ 12 አስመራጭ ኮሚቴ ተሰይሞ የምርጫ ሂደቱ ተከናውኗል፡፡

No comments