Latest

ኢትዮጵያን ለመገንባት ከአንድነት ተኳርፈን፤ ከነጻነት ተፋተን ሳይሆን በፍቅር በመደመር ወደፊት መትመም አለብን - ጠ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ



ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአዲስ አመት ዋዜማ ልዩ የበዓል ዝግጅት ላይ ባስተላለፉት መልክት የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያን ለመገንባት ከአንድነት ተኳርፈን፣ ከነጻነት ተፋተን ሳይሆን በፍቅር በመደመር ወደፊት መትመም አለብን ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዚሁ ንግግራቸውም የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በማመን በአዲሱ አመት ፕሮግራም ላይ ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት ለተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶችና የሰባዊ መብት ተመጋቾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የዘንድሮው አዲስ ዓመት ከ20 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያና ኤርትራ አንደገና በጋራ የሚከብሩት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦችና ለሌሎች ወዳጅ ሀገራት ህዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልክት አስተላልፈዋል።

ባለፉት ጊዚያት ሀገሪቱ በአስከፊ ሁኔታዎች ስር የነበረች መሆኑን ያስታወሱት ጠላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀገሪቱ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጋርጠውባት የነበረ መሆኑንና ወጣቶቹም በአመጽና በሞት ጥላ ሰር የነበሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ያለፈው ዓመት ሰባዊ ቀውስ የተባባሰበትና በተለየዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከፍተኛ ዜጎች ተፍናቅለውበት የነበረ መሆኑን አመላክተዋል።

ይሁን እንጂ በአሮጌው ዓመት መጨረሻዎች ወራት በተለይም ያለፉት አምስት ወራት የታሰሩ የተፈቱበት የተለያዩ የተገናኙበትና በሃገሪቱ አንድነት ዙሪያ መነቃቃት የታየባቸው ናቸው ብለዋል።

በዚህም ፍቅር አንድነትና መደመር በመላ ሀገሪቱ በማስተጋበት የተስፋ፣ ብርሃንና ሰላም የፈነጠቀና ሲሆን፥ ኢትዮጵያዊን ተስፋችን አንደ አደይ አበባ በማፍካት ላይ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

አዲስ አመት እያከበርን በትናንት የምንጨቃጨቅ ከሆነ ግን ዘመኑ እንጂ እኛ አልተቀየርንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊታችንን ወደ ትናንት በመዞር ወደፊት መጓዝ አንችልም ሲሉም አክለው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የጋራችን ቤት እንድትሆን አንዳችን ለአንዳችን በመደጋገፍ መስራታ ይጠበቅብናልም ብለዋል።

በአዲሱ አመት በኢትየጵያዊነቱ የሚገፋ ዜጋ የማይኖር መሆኑን ተስፋቸውን የገለጹት ዶክተር አብይ በአዲሱ ዓመት ምርጫዎችን ዴሞክራሲና እወነተኛ ለማድረግ እና ያልደረስንባቸው ከፍታዎችን ለመድረስ እንሰራለን ብለዋል።

በዚህም ከተስፋ ያለፈ ተጨባጭ ለውጥ እንዲኖርም የጋራ መግባባት ላይ መድረስና ከራሳችን መታረቅ አለብን ሲሉ አስረድተዋል።

በዓዲሱ የ2011 ዓመት የርቅና የሰላም ጊዜ እንደሚኖር ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አዲሱ ዓመት ከስርዓተ አልበኝነት ወደ ህጋዊ አሰራር የምንኘጋገረበት፣ የመንግስት ሹመኖች በስልጣን አገልጋይ የሚሆኑበት እንዲሁም ዜጎቹ በትጋታቸውና በላባቸው ተጠቃሚ የሚሆኑበት እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጎራ ላይተው አንዳቸው ሌላቸውን የማይዘላለፉበት፣ አክቲቪስቶች የነጻነት፣ ታጋዮች ሀገራዊ ብሎም አህጉራዊ አስተሳሰብ የሚያንጸባረቁበት እንዲሆንም ነው የገለጹት።

ከዚህም ሌላ ጋዜጠኞች 4ኛ የመንግስት አካል መሆናቸውን የሚያረጋግጡበትና አውነታወችን ፈልቅቀው በማውጣት ለህግ የበላይነት የሚታገሉበት እንደሚሆንም አስረድተዋል።

No comments