Latest

ኢትዮጵያ አዲስ ዓመቷን ተቀብላለች



ኢትዮጵያ አዲስ ዓመቷን ተቀብላለች

የራሷን የቀን አቆጣጠር የምትከተለው ኢትዮጵያ አዲስ ዓመቷን ተቀብላለች።

ያለፉት የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ሁነቶች ያለፉ ሲሆን፥ አዲስ ዓመትን መግባት ምክንያት በማድረግ በሚሌኒየም አዳራሽ ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ተሰናድቶም ነበር።

በዚህ ዝግጅት ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድራን እና በቅርቡ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክትም፥ ለብዙ ዓመታት ከእናት አገራቸው ተለይተው ለቆዩና በቅርቡ ወደ አገራቸው ለመጡት ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች እና ለሌሎች የዳያስፖራ ማህበረሰቦች በሙሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

አክለውም አዲሱ ዓመት የጋራ ግባችን እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ህዝባችን ለጋራ ብልጽግና ተግቶ እንዲሰራ በማስቻል የተረጋጋና ለልማት የተሰለፈ የአፍሪካ ቀንድን ዕውን ማድረግ ይሆናል ብለዋል።

አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በመላው ሀገሪቱ የተለያዩ ሁነቶች የተሰናዱ ሲሆን፥ በተለይም በአዲስ አበባ የተለያዩ የዋዜማ የሙዚቃ ድግሶች ተሰናድተዋል።

በተለይም በአዲስ አበባ የአዲስ ዓመት አቀባበሉን የርችት ስነ ስርዓት ደማቅ አድርጎታል።

No comments