መልካም ዜና! የአማራ ተማሪዎች ማሕበር ጎንደር ላይ ተመሰረተ
ጎንደር ላይ በተደረገው አጠቃላይ ስብሰባ የአማራ ተማሪዎች ማሕበር በይፋ መመስረቱ ታወቀ ።
የምስረታው ዋናው አላማ በአማራ ክልል የሚገኙት ደረጃቸውን ያልጠበቁ ትምህርት ቤቶች፣ ሜዳ ላይ ተቀምጠው የሚማሩ ተማሪዎችና ባጠቃላይ በትምህርት እና በሌሎች ጉዳዮች በአማራው ላይ የሚደረገው መድሎና መገለል እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁ የምስረታ ጉባዬ ላይ ማህበሩን የሚመሩ ስራ አስፈጻሚዎች የተመረጡ ሲሆን እነዚህም፦
- ፕሬዝዳንት ዘለቀ ምስጋናው
- ምክትል ፕሬዝዳንት የውስጥ ጉዳይ ተጠሪ አንዱለም ሸዋንግዛው
- ም/ፕሬዝዳንት የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ቴዎድሮስ ሀይሌ
- ፀሀፊ አብይ ሀይሌ
- የስርዓተ ትምህርት ጉዳዮች ተጠሪ ኪሩቤል አዲሱ(ዋና)፣ ተንሳኤ እሸቱ (ምክትል )
- የገንዘብ ያዥና ንብረት አስተዳደር ሙሉጎጃም ጀግኔ
- ስብዓዊና ዲሞክራስያዊ መብቶች ተጠሪ ኤሊያስ ውበት(ዋና)፣ ኤርሚያስ በለጠ (ምክትል )
- ባህልና ስነ ጥበብ ዘርፍ መልካሙ ፀጋዬ(ዋና)፣ ታምራት ይርዳው (ምክትል )
- የበጎ አድራጎት ዘርፍ ተጠሪ ሲሳይ አበበ(ዋና)፣ ዳኔኤል ጥላሁን (ምክትል)
- ኮምኒኬሽን ተጠሪ መሳፍንት ይህአለም (ዋና)፣ ረድኤት ማሞ (ምክትል)
- የሴቶች ጉዳይ ፈጣን ደምሌ (ዋና)፣ እመቤት ወረደ (ምክትል )
- የአባላት ጉዳይ ተጠሪ ጌታሰው በሬ (ዋና)፣ ምስክር ሸርብ (ምክትል ) አድርጎ መርጧል።
ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው |
በእርግጠኝነት ጥያቄዎቻችን ይመለሳሉ። የአማራው ጥያቄ ካልተመለሰ ሀገር መቀጠሏም አጠራጣሪ ነው። የአማራውን መደራጀት የሚቃወሙ መጨቆን የለመዱ ናቸው። እነ በረከትን ያስወገደው የአማራ ብሄርተኝነት ነው፣ ይህ ለአማራው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ትልቅ ጥቅም አለው።
ሳያምኑበትም የአማራውን መደረጃት የሚቃወሙ አሉ። ለውጥ ሲሉ ግን ይሰማሉ። የአማራ ተጋድሎ ለውጡን እንዳመጣው ግን ይዘነጉታል። በኢትዮጵያ እነ መኢሶን፣ ኢህአፓ ተደራጅተው ካመጡት በላይ አማራው መደራጀት ሲጀምር የመጣው ለውጥ ይበልጣል።
የአማራ ብሔርተኝነት ለሁሉም አስፈላጊ ነው። የአማራ ብሔርተኝነተ የገደሉትን የመግደል፣ የጨቆኑትን የመጨቆን አይደለም"
ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በአማራ ተማሪዎች ማሕበር ምስረታ ላይ የተናገረው
ምንጭ የጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የፌስቡክ ገጽ
No comments