Latest

ርግማን ሃራም ነው! (አሌክስ አብርሃም)

ርግማን ሃራም ነው! (አሌክስ አብርሃም)

ርግማን ሃራም ነው! 
(አሌክስ አብርሃም)


ሙልቅቅ
እፍፍፍፍፍስ
ጥርርርርርርርግ
ሙጥጥጥጥጥጥጥጥ
ምጥጥጥጥጥጥጥጥ


አድርጋችሁ ባዶ የድንጋይ ከምር እንደሰጣችሁን
ቋጥኝ ይናድበት ርኩስ ሃብታችሁን !
ለወሬ ነጋሪ ስማችሁ አይትረፍ
የዘመን ጨለማ በቤታችሁ ይግዘፍ
የዘረፋችሁት የደሃ አገር ጥሪት
አውሎ ነፋስ ይሁን ይብላችሁ አዙሪት !

ብየ እንዳረግማችሁ ርግማን ሃራም ነው!
ት . . . ክን !
እርርርርርርር!
ድብ. . . . ን አርጋችሁን እንደከረማችሁ
በረከት ይራቀው ደም አፍሳሽ እጃችሁ
ጸሃይ አይውጣበት ጨለማ ነፍሳችሁ

ሃይል አመንጩ ብለን በሰጠነው ጥሪት
እንዳመነጫችሁ ሃፍረትና ውርደት
የዝርፊያ ሃብታችሁ እሳት ይውረድበት !
አገሬው ላገሩ እንደሆነ እንግዳ
ተወላጅ በምድሩ እንደሆነ ባዳ
የግራችሁ ማረፊያ ምድር ትራቃችሁ
ተቅበዥባዥ ምንደኛ ሁኑ በደጃችሁ

ብየ እንዳረግማችሁ ርግማን ሃራም ነው !
እንደሲኦል ጉድጓድ ከርሳችሁ ላይሞላ
ጨካኝ መንጋጋችሁ የሚስኪኖች ተስፋ ጨክኖ እንደበላ
አባልቶ ይፍጃጅሁ አላሁ ተአላ !

ብየ እንዳረግማችሁ ርግማን ሃራም ነው !!
ብቻ
ህግ ይላክባችሁ ለጃችሁ ካቴና
ለዘረፋችሁት ያገር ባዶ ካዝና
ላስለቀሳችሁት የሚራራ እንባ አባሽ
ላሳመጻችሁት ጥሩ ፈጥኖ ደራሽ 

ይረፍና እንየው እግራችሁ ፍርድ ቤት
ጎናችሁ ከርቸሌ
አላሁ መሶሌ !!

No comments