ስንሻው የነበረው የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የግድያ ውጤት (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)
የኢንጂነር ስመኘው በቀለን፣ የግድያ ውጤት አጥብቀን ስንሻ ነበር። ዛሬም በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነን ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል በኩል አድምጠናል - "ስመኘው ራሱን አጥፍቷል...." በሚል።
የስመኘውን ሞት እውነታ ፈጣሪ ያወጣዋል ብዬ አምናለሁ፤ ነገር ግን ኢንጂነሩ ራሱን ለማጥፋት መስቀል አደባባይ ድረስ ይመጣል ብዬ አላምንም፤ ራሱን የመስቀል አደባባይ መስዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ካላሻ በስተቀር! ራስን ማጥፋት፣ የሆሊውድ ልብ-ወለዳዊ ፊልም ትርክትም አይደለ!
...ስመኘው፡- ከመሞቱ በፊት ለአማርኛው ቢቢሲ የሰጠው ቃለ ምልልስ ነበር። የሞቱ ቀንም ለጋዜጠኞች ስለግድቡ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ እንደነበረውም ሰምተናል።
ስመኘውን፣ ራሱን ለማጥፋት ያበቃው ምን ይሆን?! ...እውነት የህወሃት/የኦህዴድ/ የብዓዴንና የደህዴን/ ኢህአዴግ ቤት፤ ከሙስና የጸዳ አመራር ኖሮት ይሆን? የአሁኖቹን ጭምር! ...ህምምምምም
ኢንጂነሩ፣ ለሙሰኞች መረጃን በመሸፈን ከለላ ሆኗል ብለን ብናምን እንኳን (አይሆንም ባልልም) ፤ ራሱንና ቤተሰቡን መጥቀም ያልቻለ ግለሰብ፣ ለሙሰኞች ብቻ አገልጋይ ይሆናል ብሎ ማሰብ የዋህነት ይሆናል።
....በዚህ አካሄድ፣ የሰኔ 16 ቱ የመስቀል አደባባይ የቦንብ ፍንዳታም፤ "ቦንቡ ራሱ የፖሊስ መኪናን እያሽከረከረ፣ መስቀል አደባባይ ላይ ደርሶ ፈንዳ" የሚል የፖሊስ ምርምራ ውጤት ሊያሰማን ይችል ይሆናል!
በኢህአዴግ ቤት፣ መረጃ እንደአመቺነቱ ትርፍና ኪሳራው ተሰልቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አሁንም እየተማርን ነው! ....
...የአሁኑን የኢህአዴግ አመራር እንቅስቃሴም፤ በትኩረት እና ይበልጥ ንቁ በመሆን ልንከታተለው ግድ መሆኑን፣ የስመኘው የሞት ሽፍንፍን ትርክት መልስ ሰጪ ነው!
ነፍስ ይማር፣ ፈጣሪ የሟችን እውነት ያውጣ!
ኢትዮጵያ!
No comments