Latest

የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና ጥቅም ለአሁኗና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ - ክፍል ~ ፪ (ከፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ )

የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና ጥቅም ለአሁኗና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያኒዝምን ያዩት እንደ መንፈሳዊ ጎዳና ከእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር በቀጥታ መንገድ ከፋች፤ ሌላው ደግሞ ኢትዮጵያ የጥቁር ሐገር ሆና እራሷን ማስተዳደር የቻለች ታላቅና ክቡር እንዲሁም የራሳችው ሐገርና እንደ አለኝታ በመቁጠር ነበር የኢትዮጵያኒዝምን ፍልስፍና በመንፈሳዊ ትግል የጀመሩት፤ ያነፁትና የገነቡት።

የሚገርመው የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና መንፈሳዊ መሠረት ይኑረው እንጂ ለተጨቆኑት የዓለም ሰዎች ሁሉም መመሪያ አድርገው ነው የመሠቱት። ከመንፈሳዊ መሠረቱ ወደ ዓለማዊ ጭቆናዎችን ለመቋቋም የኢትዮጵያኒዝም የሚከተሉትን ስምንት ባሕሪያት ያጠቃልላል፤

  1. መንፈሳዊ ነፃነት 
  2. በራስ መተማመን 
  3. ለራስ ክብር 
  4. እራስን መቻል 
  5. የውጭ ጭቆናን መቋቋም 
  6. መንፈሳዊ ነፃነት ከዓለማዊ ነፃነት ጋር ማጋራት አብሮ እንዲሔድ ማድረግ . 
  7. ተጨቆኑ ሰዎች በጋራ መተባበር 
  8. ሰብአዊነት፣ መረዳዳትና እርስበርስ መተሳሰብ። 
እነዚህ ስምንት ታላላቅ ፅንሰ ሀሳቦች የኢትዮጵያኒዝምን ፍልስፍና የሚያራምዱና በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያኒዝምን ተከትሎ የመጣውን ፓንኣፍሪካኒዝምን ለአፍሪቃ ነፃነት አንድነት ሕድስና ስር መሠረት የሰጡ ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ፅንሰ ሀሳቦች ናቸው። የኢትዮጵያ ነፃነትም ጠቅሟል።

እንግዲህ ኢትዮጵያኒዝም በ16ኛው ክፍለ ዘመን ተጀምሮ 18ኛው ክፍለ ዘመንን ተደግፎ እሰከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የቆየ ፍልስፍና ነው።8 ኣሁንም ቢሆን የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ታቦይ ኢምቤኪ እንደሚሉት የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና አሁን ላለንበት ዘመን ያስፈልጋል ይላሉ።9

እናም የኢትዮጵያ ቤተክርስትያኖችም በደቡብ አፍሪቃ በአሜሪካና በካሪቢያን ሀገሮች አሉ፤ አሁንም ቢሆን እነዚህ ቤተክርስትያኖች ከመንፈሳዊ አገልግሎት በተጨመማሪ ያላለቀውን የነፃነት ትግል የገለፁ ናቸው። ኢትዮጵያኒዝም በዓለም መድረክ ያመጣቸው ለውጦች በደቡብ አፍሪቃ የአፍሪቃን ናሽናል ኮንግሬስ ያቋቋሙት በደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ቤተክ/ ቄሶች ናቸው፤ እናም የመጀመሪያው የአፍሪቃ ናሽናል ኮንግሬስ ፕሬዝዳንት ጆን ላንጋቢሌሌ ዱቤ በኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍናቸውና አቋማችው ታስረው ከተፈቱ በኋላ የአፍሪቃ ናሽናል ኮንግሬስ ፕሬዝዳንት ሆነዋል።

የስማቸው ቅፅል ግልፅ ኢትዮጵያዊ ሁልጊዜ አደጋ ላይ ያሉ ይሏቸው ነበር፤ እናም ነጮቹ 1906 የኢትዮጵያኒዝምን ፕሮፖጋንዳ አንቋሽሸው ኢትዮጵያኒስትን ማሰርና አልፎ አልፎም መግደል ጀመሩ። ቀጥለውም የኢትዮጵያኒዝም እንቅስቃሴን እንደ አደጋና እንደ ረብሻ አሰራጭ ቆጥረው የወታደር ኃይላቸውን አሳደጉ።

የዙሉ እንቅስቃሴ 1906 ቀጥሎም ባንባታ በሌሎችም አካባቢዎች ያፓርታይድ ተቃውሞ እንቅስቃሴ ተጀመረ። እንቅስቃሴውውንም ያስጀመሩት እንዲሁም ይመሩት የነበሩት ኢትዮጵያኒዝሞች ነበሩ። እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪቃ ሐገሮች በእንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ፖርቱጋል፣ በቅኝ ግዛት ተገዝተው የነበሩ በኢትዮጵያኒዝም በመጠቀም ሃይማኖትን ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ተጠቅመውበታል። ራስተፈሪያኒዝንም የፈለቀው ኢትዮጵያኒዝም በሚለው ፍልስፍና ነው።

አፍሪቃ ለአፍሪቃዊያን የሚለው አስተሳስብ የመጣው ኢትዮጵያኒዝም በሚለው ፍልስፍና ነው። ቅኝ ግዛትን በመቃወም እነፕሬዝዳንት ጆሞ ኬኒያታ ሳይቀሩ በኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና እሰከ 1960 ዓ.ም ድረስ ተጠቅመውበታል። በተለያየ መንገድ ቢገለፅም የተለያዩ ሰዎች በተለያየ መንገድ ቢጠቀሙበትም መሠረታቸው ኢትዮጵያኒዝም እንደ ሆነና አፍሪቃን ሙሉ ከቅኝ ግዛት ለማውጣት እንደ ችቦ መብራት እነደ ተጠቀሙብት ጥርጥር የለውም። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያኒዝም የኢትዮጵያ ሚና በኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና ምንድነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።

ይቀጥላል... 

No comments