Latest

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ከሀላፊነታቸው ተነሱ።

ኢንጂነር አዜብ


(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ከሀላፊነታቸው ተነሱ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ቦርድ በትናንትናው እለት ባካሄደው ስብሰባው ኢንጂነር አዜብ አስናቀን ከሀላፊነት ማንሳቱን ምንጮች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል።

በምትካቸውም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ ኢኒስቲቲዩት ዳይሬትከር የነበሩት ዶክተር አብረሃም በላይ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

No comments