Latest

እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የላውሮ ግምት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የላውሮ ግምት - ቢቢሲ

እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የላውሮ ግምት እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የላውሮ ግምት

ሁለቱ የፕሪሚየር ሊጉ አዳዲስ አሰልጣኞች በዚህ ሳምንት እርስ በእርስ ይጫወታሉ። ቅዳሜ የቼልሲው ማውሪዚዮ ሳሪ በሜዳቸው የአርሴናሉን ኡናይ ኤምሬን ያስተናግዳሉ።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን አርሴናሎች ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ሲቲ ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ "አራተኛ ሆነው ያጠናቅቃሉ ማለቴን በድጋሜ ላጤነው እችል ይሆናል" ብሏል።

ላውሮ ዘንድሮም 380ዎቹንም የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች በሙሉ ይገምታል።



የላውሮ ግምቶች

ቅዳሜ


ካርዲፍ ከኒውካስል

ካርዲፎች ባለፈው ሳምንት በበርንማውዝ ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ ተሻሽለው እንደሚቀርቡ አስባለሁ።

በቶተንሃም ቢሸነፉም ኒውካስሎች ጥሩ የተንቀሳቀሱ ሲሆን በዚህ ዓመት የሚቸገሩ አይመስለኝም።

የላውሮ ግምት: 1-1


ኤቨርተን ከሳውዝሃምፕተን

የኤቨርተን ደጋፊዎች ማርኮ ሲልቫ በሚመርጡት አጨዋወት ደስተኞች ሲሆኑ፤ በሜዳቸው በሚያደርጉት ጨዋታ ውጤቱ ምንም ይሁን በከፍተኛ ሁኔታ ይደግፋሉ።

ከበርንሌይ ጋር በነበራቸው ጨዋታ አጥቂያቸው ዳኒ ኢንግስ በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይሮ ከገባ በኋላ ጥሩ መንቃሳቀስ ቢችሉም ይህን ጨዋታ የሲልቫ ቡድን እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት: 2-0


ሌስተር ከዎልቭስ


ሌስተሮች በመጀመሪያ ጨዋታቸው ከማንቸስትር ዩናይትድ ጋር ጥሩ የተንቀሳቀሱ ሲሆን ጂሚ ቫርዲም ጎል ማስቆጠር ችሏል።

ዎልቭሶች በበኩላቸው በኤቨርተን ሁለት ጊዜ ከመመራት ተነስተው አቻ መለያየት ችለዋል።

የላውሮ ግምት: 2-1


ቶተንሃም ከፉልሃም


ቶተንሃሞች ጥሩ ተንቀሳቅሰው ኒውካስልን ያሸነፉ ሲሆን ላልተወሰነ ጊዜ በዌምብሌይ መጨዋታቸው የሚያሳስባቸው አይመስለኝም።

ፉልሃሞች በዚህ ሳምንትም ሌላ ለንደን ክለብን ያገኛሉ። ባለፈው ሳምንት በክሪስታል ፓላስ የተሸነፉ ሲሆን በዚህ ሳምንትም ነገሮች ቀላል አይሆኑላቸውም።

የላውሮ ግምት: 2-0


ዌስት ሃም ከበርንማውዝ


አዲሱ የዌስት ሃም አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሪኒ ብዙ አጥቂዎችን ገዝተው ጥሩ ቡድን ለመስራት ቢጥሩም የተከላካይ መስመራቸው ግን አስጊ ነው።

በርንማውዞች ከሜዳቸው ውጭ ጠንካሮች ባይሆኑም ነጥቦችን እያገኙ ነው። ከዚህ ጨዋታም አንድ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት: 1-1


ቼልሲ ከአርሴናል
የአርሴናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ምርጥ ቡድናቸውን ለማግኘት ብዙ መስራት አለባቸው።

አርሴናሎች ባለፈው ሳምንት ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ሲቸገሩ ቼልሲ በቡኩሉ በቀላሉ ነበር ሃደርስፊልድን ያሸነፈው።

የላውሮ ግምት: 2-0

እሑድ



በርንሌይ ከዋትፎርድ
የሚያገኙትን ዕድሎች የሚጠቀሙ ከሆነ በርንሌይዎች ይህን ጨዋታ በጠባብ ውጤት የሚያሸንፉ ይመስለኛል።

ዋትፎርዶች ወጥ አቋም ባያሳዩም ብዙ ቡድኖች ከእነሱ በታች ሆነው የውድድር ዓመቱን እንደሚያጠናቅቁ እገምታለሁ።

የላውሮ ግምት: 1-0



ማንቸስተር ሲቲ ከሃደርስፊልድ
ማንቸስተር ሲቲዎች በጉዳት ያጡትን ኬቪን ደ ብሩይንን የሚተኩላቸው ብዙ አማራጫችን ይዘዋል።

ሃደርስፊልዶች ባለፈው ሳምነት በቼልሲ በሰፊ ውጤት የተሸነፉ ሲሆን በዚህ ሳምንትም ኢትሃድ ስታዲየም ላይ ከዚህ የተለየ ነገር ይጠብቃቸዋል ብዬ አልጠብቅም።

የላውሮ ግምት: 3-0



ብራይተን ከማንቸስተር ዩናይትድ
የብራይተኑ አሰልጣኝ ባለፈው ሳምንት በዋትፎርድ ሲሸነፉ ካልተጠቀሙባቸው አዳዲስ ተጫዋቾች መካከል አንዳንዶቹን በዚህ ጨዋታ ያሰልፋሉ።

ማንቸስትር ዩናይትዶች ባለፈው ሳምንት ሌስተርን ለማሸነፍ በቂ ጨዋታ ያሳዩ ሲሆን ኮከብ ተጫዋቾቻው ወደ ሙሉ ብቃት ስለሚመለሱ እየተጠናከሩ ይሄዳሉ።

የላውሮ ግምት: 1-2

ሰኞ



ክሪስታል ፓላስ ከሊቨርፑል
ሊቨርፑሎች ባለፈው ሳምንት የዌስት ሃም ተከላካይ መስመር የፈጠረላቸውን አይነት ክፍተት በደቡብ ለንደን አያገኙም።

የፓላሱ አሰልጣኝ ሮይ ሆድሰን በሚመርጡት አጨዋወት መሠረት ምንም ክፍተት የማይፈጥሩ ሲሆን ጨዋታውንም ተቀራራቢ ያደርጉታል።

የላውሮ ግምት: 1-1

No comments