Latest

በኢ/ር ስመኘው ግድያ የሜቴከና ህወሓት እጅ አለበት! (ስዩም ተሾመ)


ሰኞ ዕለት ጠ/ሚ አብይ አህመድ "የህዳሴ ግድብ አሁን ባለው አካሄድ የዛሬ አስር አመት አይጠናቀቅም" ማለቱ ይታወሳል፡፡ 

ትላንትና ደግሞ የመብራት ሃይል ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ከመከላከያ ኢንጂነሪግ እና የህወሓቶች ዘረፋ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነት ሊነሱ እንደሆነ ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል፡፡ 

በዚህ መሠረት የዶ/ር አመራር የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ የግንባታ ሂደቱ እንዳይፋጠን ዋና ማነቆ የሆኑትን የመከላከያና ህወሓት ባለስልጣናት ከቦታው ጠራርጎ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ 

ከዚህ አንፃር ኢንጂነር ስመኘው ብዙ ሚስጥር ያወጣል፡፡ ስለዚህ ኢንጂነሩ ይህን ከማድረጉ በፊት የመከላከያና ህወሓት ገድለውታል ወይም አስገድለውታል፡፡ ከዚህ በፊት ወዳጄ William በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጥልቅ ትንታኔ የያዘ ፅሁፍ አውጥቶ ነበር፡፡ 

በዚህ ፅሁፍ ለግድቡ ግንባታ መጏተት ዋናው ምክንያት በዶ/ር #ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቦርድ እና #የሜቴክ ጄኔራሎች መሆናቸው በግልፅ ጠቅሶ ነበር፡፡ ይህን ባደረገ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሀገሩ እንግሊዝ ተጏዘ፡፡ ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ ሲል ቪዛ ተከለከለ፡፡ 

ይህ ጋዜጠኛ ከሞት የተረፈው እንግሊዛዊ በመሆኑና ቢሞት ከሀገሪቱ የውጪ ደህንነት መስሪያ ቤት (MI6) ምላሹ የከፋ ስለሚሆን ብቻ ነው፡፡ ጋዜጠኛው እውነታውን በመዘገቡ ምክንያት ይህን ካደረጉ ሙሉ መረጃውን በተግባር የሚያውቀው ኢንጂነር ስመኘውን ደግሞ ከመግደል ውጪ አማራጭ የላቸውም፡፡ 

ይህን ያደረጉት ደግሞ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የተመደበውን ገንዘብ ሲዘርፉ የኖሩት የመከላከያና ህወሓት ባለስልጣናት ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት ኢንጂነሩ ለደህንነቱ በመስጋት ወደ ውጪ ሀገር ለመሸሽ ሞክሮ የነበረ መሆኑ፣ እንዲሁም አንዳንድ የህወሓት አፈ-ቀላጤዎች ደግሞ ቀድመው ሙሾ ሲያወርዱ የነበረ መሆኑ ጠቋሚ ነው፡፡

No comments