Latest

ለጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ የተፃፈ ደብዳቤ። (በላይ በቀለ ወያ)


መልእክት እንዳናደርስ፣ በስልኮት አፍ በኩል
ቁጥሮትን አናውቀው
ወይ እንዳንደውል፣ ወይ እንዳንመሰኩል
ጉዳይ እንዳንነግሮ ፣ የለንም ኢሜሎ
ገዳይ ጉዳይ ሲሆን
እንደው የኛ  ጩከት ፣  ሲሆን    "ማሎ ማሎ "
ተገቢ ባይሆንም
በኢንተርኔት ዘመን ፣ ደብዳቤ ፃፍንሎ።
።።።
እንደምኖት አብይ ፣
እኛ አለን በስጋት ፥ እርሶን ስንደግፍ
ባይቀርልን እንኳ ፣ ይቀራል ያልነው ግፍ
አለን ተደምረን
ሀገር ክንፍ አውጥታ
መብረር እንድትችል ፣ እግራችንን ሰብረን
ትንሳኤዋን ልናይ ፣ ነፍሳችን ገብረን
አለን ስናነክስ
አለን ስናለቅስ ፣ መኖር እያማረን ።
።።።
እናምሎት አብይ
እርሶ ወደ ስልጣን ፣ ከመጡ በኋላ
ጥላቻ እንደ ጥላ
ብለን ነበር ያልፋል
ነገር ግን እያደር ፣ጭራሹን ይገዝፋል።
እርግጥ ነው
እውነት ነው
ካምናና ካቻምና ፣ ስናነፃፅረው
በገፍ እና በግፍ ፣ ግፈኛ ያሰረው
ብዙ ሰው ተፈቷል ፣ ዘንድሮ ጥሩ ነው
ዘንድሮ መልካም ነው
በጥቂቱም ቢሆን ፣ ተቀርፏል ጭቆና
የሆነው  ሆነና
ዛሬም ሰው ይሞታል ፣ ሲወጣ አደባባይ
ዛሬም ቁጭት አለ ፣ በነጠላ ጫፍ ላይ
አገገምን ስንል
አልተገላገልንም ፣ መርቅዟል ህመሙ
እኛ የምኖሎት
በተገዳዮች  ፊት  ፣ ገዳይ ከሸለሙ
በተበዳዮች ላይ  ፣ በዳይን ከሾሙ
ምንድነው ይቅርታ
ምንድነው ምህረት
የመደመር ሀሳብ ፣ ምንድነው ትርጉሙ ?
።።።።
እንደምኖት አብይ  ፣ እንዴት ነው ስልጣኖ
ገለታ ዋቀዮ ፣
እየተደመርን ፣  አለን በተቃርኖ
ሽፈራው ደና ኖ ፣ ያ ለማ ደና ኖ
እኛ ሚኒላችሁ
ኢየተቀነሱ ፣ መደመር ሚንዲኖ?
ሚንዲኖ እዛ እዚህ ፣ ሰው ሚፈናቀሎ
ሚንዲኖ እዛ ኢዚ ፣ ሰው የሚገደሎ
ሚንዲኖ ፀጢታው ፣ ሚንዲኖ ሁካታው
ሚን አይነት ፂድቅ ነው
ቀኝ ጉንጪን መስጠት ፣ ግራ ለሚማታው
ግራ ጉንጪን ደጊሞ
ግራ መጋባቱ ፣ ጢቂሙ ሚንዲኖ
ፊቂር ለማይገባው
ፊቂር እየሰጡ ፣ የሚን መታገስ ኖ
ጊራ ጉንጪን ላለ
ጊንባር ቀደሙ መልስ ፣ ጊምባሩን ማለት ኖ
እውነታችንን ኖ!!!
።።።።።።።።
እንደምኖት አብይ ፣ እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን ፣ የፍቅር ጎዳና
እየተመለስን
ተገነቡ ሲባል እየፈራረስን
ተደመርን ስንል እየተቀነስን
እየተጎናተል  ፣ በዘር ጅኒ ጃንካ
ዛሬ አለን በስጋት
ነገ ሚሆነውን ፣ ዋቀዮ ሲቤካ።
።።።
እኛ የምንሎት
ከካቻምና በፊት
የነበረን ገዢ ፣ ካቻምና ወቀስን
አምና ስልጣን ያዝን
የካቻምናዎችን ፣ ደም እያፈሰስን
ዘንድሮ በብልሀት  ፣ ዙፋኑን ወረስን።
ሰይጣኑ ሳይጠፋ
ስልጣኑን ቢይዙት ፣ መች እኛን ፈወሰን
ደም የጠማው ወንበር
በፍቅር ሲያጠምቁት ፣ ደንብሮ ጨረሰን።
እናም የምንሎት
በፍቅር ሲጠመቅ
አልለቅም ያለውን  ፣ ፀብ መጥመቅ ያዋጣል
አንዳንዴ አጋንንት
አጋንንቱን ስቦ ፣ በአጋንንት ይወጣል ።
።።።።።
እንደምኖት አብይ ፣ እንዴት ነው ስልጣኖ
ፍቂሪና ሚሂረት ፣ በእርግጥ ጢሩኖ
ጊን ደሞ ጊን ደሞ
ሲበዛ ዪመራል ፣ ኣይደለም ተገቢ
ኢንኳንስ የሰው ሊጅ
ጊፍን ለሚያበዛ  ፣ አዪራራም ረቢ።
እኛ የሚንሎ
ተገነባን ሲንል ፣ የሚንደን ቶሎ
ተደመሪን ሲንል ፣ ለሚያጎድለን ጎድሎ
አሊጠግብ ላለ አካል
እንባ ደማችኒን ፣ ላባችንን መጦ
ለሱ ሰላም ሲባል ፣ ኢኛን አበጣብጦ
ለመኖር የሚጢር ፣ ሀገሩን በታቲኖ
ሆዲን  ለሚያሰፋው ፣ ምዲሩን ሸንሺኖ
ፊርድ ካልሰጠኖ
ሚህረት ሚንዲኖ
ኢቂርታ ሚንዲኖ
የመደመር ሀሳብ ቲርጉሙ ሚንዲኖ?
እናም እናምሎ
ኢኛ የምንሎ
በፊቂሪ ሲያጠምቁት
አሊለቅ ያለን ጋኔን ፣ ፀብ መጢመቅ ያዋጣል
ጨለማ ውስጥ ሆኖ
ፀሐይ ለሰረቀ ፣ ማን ምህረት ይሰጣል?!

No comments