Latest

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችን ለሚፈጥሩ አካላት የመጨረሻ ነው ያሉትን የሰላም ጥሪ አቀረቡ ፡፡


የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችን ለሚፈጥሩ አካላት ወደ ሰላም እንዲገቡ የመጨረሻ ነው ያሉትን የሰላም ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም በሚያሳፍር ሁኔታ ሰዎች ይሞታሉ በማለት ንግግር ያሰሙ ሲሆን ይህ እንዲያበቃም "እባካችሁ ወደ ሰላም ግቡ፤ ይህ የመጨረሻ የሰላም ጥሪዬ ነው" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ እና በአስመራ መካከል ያለው የጥላቻ ግንብ መናዱን አንስተው በአንዳንድ ክልል ያለው "የሳር ቀጤማ ግንቦች ይፍረሱ" በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የዛሬው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይዘው የመጡት ፍቅር በ50 ቢሊየን ብር የማይገዛ ውድ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የሰላም ዋጋው ያልገባቸው አካላት አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እያስነሱ መሆኑን ጠቅሰው እስቲ  ዛሬ እንኳ ስለ ሰላም ተማሩ ብለዋል በንግግራቸው፡፡

 ኢትዮጵያ ወስጥ የሰዎች ሞት ማብቃት አለበት ሲሉም  የሰላም ጥሪያቸውን አጽንዖት  አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አልፎ አልፎ የምታውኩን ሰዎች ፍቅራችንን ባታበላሹት መልካም ነው ነግርግን ግጭቶች በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ ሰውነንና ወዳልተፈለገ ነገር እንዳታስገቡን አደራ እላለው ብለዋል፡፡

No comments