ለዶክተር አብይ ድጋፍ በራያ የተጠራው የድጋፍ ሰልፍ በህወሐት ታጣቂዎች በኃይል ተበተነ
የዶክተር አብይን የለውጥ ጅምር ለማሞገስ ትናንት በራያ የተጠራው የድጋፍ ሰልፍ በህወሐት ታጣቂዎች በኃይል ተበትኗል።
የትንሳኤ ወኪል ከስፍራው እንዳጠናቀረው ሪፖርት፣ በአላማጣ፣ በዋጃ እና በቆቦ ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ እንዳይደረግ የአካባቢው አስተዳደር ቢከለክልልም፣ ህዝቡ በራሱ ኃላፊነት ወደ አደባባይ በመውጣት ለዶክተር አብይ ያለውን ድጋፍና በህወሀት አስተዳደር ላይ ያለውን ተቃውሞ አሰምቷል።
በሰልፎቹ ጥያቄዎች ስጋት የገባው የአካባቢው የህወሀት አስተዳደር በአድዋው የመከላከያ ሹም በኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር አዛዥነት ሕዝቡን በኃይል እንዲበተን አድርጓል።ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል።
የተለያዩ ሞዴል የሆኑና የተሽከርካሪ ባለቤቶች ማረጋገጫ ደብተር ሊብሬ የሌላቸው 120 አውቶብሶች በአንበሳ የከተማ አውቶብስ ድርጅት ውስጥ መገኘታቸው ተዘገበ። ይህ ማለት ሙሰኞች ከሥራ ኃላፊዎች እና ከሹመኞች ጋር በመመሳጠር የግላቸውን 120 አውቶቡሶች የአንበሳ አውቶቡስ ዐይነት ቀለም አስቀብተውና ቁጥር ሰጥተው ልክ እንደ አንበሳ አውቶቡስ ነዳጅ በነጻ እያስቀዱ እና እየነገዱ የሀገር ሀብት ሲበዘብዙ ከርመዋል ማለት ነው።
ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቄ ከ20 አመት በኋላ አዲስ አበባ ሲገቡ እና ሀዋሳን ሲጎበኙ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የኤርትራው መሪ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን እና ፕሬዚዳንቱን ዶክተር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ተቀብለዋቸዋል።
በአቀባበል ሥነ ስርአቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ያልተገኙት ዛሬ በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚበረከትላቸውን የክብር ዶክትሬት ለመቀበል ወደዚያ በማምራታቸው እንደሆነ ታውቋል።
ኢህአዴግ -የሶማሌ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር- በቀድሞው የደህንነት ሹም ላይ ያቀረቡትን ክስ አላውቀውም አለ።
አቶ አብዲ በመግለጫቸው የቀድሞውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን '' ሙሰኛ፣ ሌባ እና ራሰ ወዳድ ነው'' በማለት ከሰዋቸዋል።“አቶ ጌታቸው ለላፉት 27 ዓመታት ለምን ከሚዲያው ተደብቆ ቆየ? የአሜሪካው የስለላ ተቋም ኃላፊ እንኳ ህዝብ ፊት ወጥቶ መግለጫ ይሰጣል።
አቶ አብዲ በመግለጫቸው የቀድሞውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን '' ሙሰኛ፣ ሌባ እና ራሰ ወዳድ ነው'' በማለት ከሰዋቸዋል።“አቶ ጌታቸው ለላፉት 27 ዓመታት ለምን ከሚዲያው ተደብቆ ቆየ? የአሜሪካው የስለላ ተቋም ኃላፊ እንኳ ህዝብ ፊት ወጥቶ መግለጫ ይሰጣል።
እሱ ተንኮል እየሰራ ካልሆነ በቀር ለምን ተደበቀ?'' ሲሉም ጠይቀዋል።ይሁንና አቶ ጌታቸው ያደርሱባቸው የነበረውን በደል ለሁሉም የኢህአዴግ ማዕከላዊ የኮሚቴ አባላት አቤት ብያለው'' ቢሉም፤ ኢህአዴግ ግን ምንም አቤታቱ አደረሰኝም ብሏል።
እነዚህንና ሌሎችንም ወቅታዊ መረጃዎችን አጠናቅረን በሰዓቱ ወደ እናንተ ደርሰናል።
ትንሳኤ- የእርስዎ ራዲዮ!
No comments