የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' -ቢቢሲ
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከ3ሺ የሚልቁ የዩኒቨርስቲ መምሕራንን ቤተ መንግሥት ጋብዘው ውይይት አካሄደዋል።
በስብሰባው መሐል ዘና የሚያደርጉ ሁኔታዎች አልጠፉም።
በመሐል ጥያቄዎች እየተጠየቁ በፍቃደኝነት ወደ መድረክ የሚወጡ ሰዎችን ጋበዙ። ስምንት መምህራን ወደ መድረክ ከወጡ በኋላ የ'ፑሽ አፕ' ውድድር ተካሄደ። ሳይደክሙ በርካታ 'ፑሽ አፕ' በጽናት የሠሩ ሦስት መምህራት ወደ ቻይና ለ15 ቀን ሥልጠና እንደሚሄዱ አብስረዋቸዋል።
ቆየት ብለውም ሁሉም ወደ መድረክ የወጡ መምህራን የዚሁ እድል ተሳታፊ እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከመምህራኑ ጋር አብረው እየሠሩ፣ ጎን ለጎን ስፖርቱን በትክክል የማይሠሩትን መምህራን ይከታተሉ ነበር ብለዋል ተሳታፊዎች።
በተመሳሳይ ሴት መምህራንን ወደ መድረክ ሲጋበዙ በርካታ ሴቶች እድሉን ለመጠቀም ወደ መድረክ የወጡ ሲሆን ለሁሉም የቻይና ጉብኝት ዕድል ሰጥተዋቸዋል።
የ 'ፑሽ አፕ' ጉዳይ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሰፊ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን አንዳንዶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ማድረጋቸው ምቾት እንዳልሰጣቸው ሲገልጹ ሌሎች ደግሞ መምህራኑን እንዴት ማስተማር እንዳለባቸው በድርጊት ለማስተማር ያደረጉት ነው ሲሉ ተከራክረዋል።
የፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ዘግይቶ መምጣት
መድረኩ ከሞላ በኋላ ዘግየት ብለው የመጡት ፕሮፌሰር በየነ ወደ ፊት ወንበር እንዲመጡ የጋበዟቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነበሩ ብለውናል ተሳታፊዎች። ፕሮፌሰሩ ወደፊት ሲራመዱም የመምህራኑ ደመቅ ያለ ጭብጨባ እንዳጀባቸው ያስተዋሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ተፎካካሪ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ይሄ ጭብጨባ ፕሮፌሰሩ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንጂ ለምርጫ አይደለም መቼም ሲሉ ቀልደዋል።
የ42ቱ መምህራን ጉዳይ
ከ25 ዓመታት በፊት ባንጸባረቁት አመለካከትና ባነሱት የአካዳሚያዊ ነጻነት ምክንያት ከዩኒቨርስቲ የተባረሩ መምህራን ወደ ሥራ ገበታቸው ለመመለስ መንግሥት ዝግጁ እንደሆነ አቶ ዐብይ አሕመድ መጥቀሳቸውን አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጠቅሰዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለትምህርት ጥራት ጋሬጣ ናቸው ተብለው ከተጠቀሱ ጉዳዮች አንዱ ፖለቲካዊ ሥራ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሰተት ብሎ መግባቱ እንደሆነ ተነስቷል። የመመህራንና የተማሪዎች የአንድ ለአምስት አደረጃጀትም እንደ መነሻ ተጠቅሷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ዋናው ችግር የፖለቲካው ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት ሳይሆን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዳካማ ሆነው ወደኋላ እየተጎተተ መሆናቸው ነው ብለዋል። የከፍተኛ ትምህርት አቅምና ተጽእኖ ፈጣሪነት መላላት ነው ችግሩ ሲሉ ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠታቸውን ያነጋገርናቸው ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

የውይይቱ ትኩረት
በዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትሩና የዩኒቨርስቲ መምህራን ውይይት በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን የትምህርት ጥራት፣ የተቋማት ግንባታ፣ የኑሮ ውድነት፣ የኤርትራ ጉዳይና ሌሎች በርካታ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በጥያቄ መልክ መነሳታቸውን ተሳታፊዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ለስብሰባ ተሳትፎ የተመረጡ መምህራ በተለያየ መንገድ ዩኒቨርስቲያቸውን እንዲወከሉ የተመረጡ ሲሆን አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በምርምርና ማስተማር ጎላ ያለ ነጥብ ያስመዘገቡ መምህራንን ለስብሰባው መርጠው መላካቸውን፣ ሌሎች ደግሞ በድምጽ ብልጫ መምህራኑን ልከዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ጥላዬ ጌቴ አጭር ማብራሪ ካቀረቡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ መድረክ የጋበዟቸው ሲሆን ዶክተር ዐብይ አሕመድ በበኩላቸው በብዛት እናንተን መስማት ነው የምፈልገው ብለው ተሳታፊዎችን ለጥያቄ እንደጋበዙ ተገልጿል።
ከአክሱም ዩኒቨርስቲ የተወከለው መምህር ሙሉ ማእሾ ለቢቢሲ እንደተናገረው ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰፋ ያለ ገለጻ በማድረግ የሚታወቁ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ግን በቀጥታ ወደ ተሳታፊዎች እንዳመሩ ተናግሯል።
"ዛሬ ብዙ አላወራም፥ ከናንተ ለመማር ነው የምፈልገው፣ ሐሳቦቻችሁን እንደ ግብአት እንድጠቀምባቸው" ብለው ለተሳታፊዎች እድል ሰጥተዋል። ተሳታፊዎችም በነጻነት የሚሰማቸውን ተናግረዋል።
ውይይቱ ከትምህርት ጥራት ባሻገር የአገር ደህንነት፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ሉአላዊነት ላይ ሐሳቦች ተንሸራሽረውበታል።
በኤርትራ ጉዳይ ከባድመ በፊት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ እንዲቀድም የተፈለገበትን ምክንያትም ዶክተር ዐብይ ለመምህራቱ አብራርተዋል።
የትምህርት ጥራትን በተመለከተም ፍኖተ ካርታ እየተዘጋጀ እንደሆነና ከፍ ያለ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራበት፣ በመጨረሻም ወደ መምህራኑ ወርዶ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግበት መናገራቸውን፣ "ብዙዎቹ ጥራትን የተመለከቱ ዛሬ የተነሱና ጥያቄዎችም ሆኑ ስጋቶች" በዚሁ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ አማካኝነት እንደሚመለሱ መግለጻቸውን ዶክተር ፍሬው አሞኘ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) መጋበዙን በተመለከተም ጥያቄ መነሳቱንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የድሀ ሉአላዊነት አለመኖሩን፣ እኛ ባንፈልግም ያደጉ አገራት መንግሥታት ምን እየተካሄደ እንደሆነ እኛ ባናውቅም እነሱ ያውቃሉ ሲሉ የሉአላዊነት ጉዳይ ላይ ማብራራታቸውን ከወለጋ ዩኒቨርስቲ የተሳተፈው አቶ ተፈሪ ፍሪሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"መድረኩ ሰፊ ጊዜን ለመምህራን የሰጠ፣ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ምክረ ሐሳቦችን ጭምር እንዲያነሱ የፈቀደ ደስ የሚል መድረክ ነበር" ብለዋል የባህር ዳሩ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው አሞኘ።
ውይይቱ ከጠዋት እስከ ምሳ ሰዓት የዘለቀ ነበር።

No comments