Latest

“ከእንግዲህ ኢትዮጵያ ጥቂቶች የሚፈነጩባት፣ብዙሀን የሚያለቅስባት ምድር አትሆንም” አቶ ደመቀ መኮንን።

ባሕር ዳር ታላቁን ሰልፍ በሰላም አጠናቃለች።

‹‹አንድ መሆናችን እንቅልፍ የነሳቸው፣ ያልታደሰውና የአሮጌው ዘመን ቁማርተኞች ከእግራችን እየተከተሉ ሰላማችን ለማወክ እየጣሩ ነው፤ ይሁን እንጂ አልተሳካላቸውም!›› አቶ ገዱ አንዳርጋቸው።

“ከእንግዲህ ኢትዮጵያ ጥቂቶች የሚፈነጩባት፣ብዙሀን የሚያለቅስባት ምድር አትሆንም” አቶ ደመቀ መኮንን።

"ተቀዋሚዎች ወደ ሀገር እየገቡ ያሉት የሽግግር መንግስት ሊመሰረት ነው?ወይስ ባለው ሊቀጥሉ?"

የባህር ዳሩ ሰልፍ እንግዳ ወይዘሮ እማዋይሽ በሰንደቅ ዓላማ ዙሪያ ከሕዝብ ጋር ሰፊ ውይይት ሊኖር እንደሚችል ተጠቆመ።የሰንደቅ ዓላማው ውዝግብ ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድንም በጣም እያሣሰቧቸው ካሉት ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ተጠቅሷል። በመሆኑም “በዚህ ዙሪያ ያሉ የተለያዩ የህዝብ ፍላጎቶችን እንዴት መፍታት ይቻላል?” በሚለው ዙሪያ ጥናት የሚያደርግ ቡድን ለማቋቋም የታሰበ ሲሆን እስከ ታች ድረስ የሚወርድ ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በታላቅ የውጭ ጋዜጦችና መጽሄቶች ሰፊና አዎንታዊ ሽፋን እያገኙ ሲሆን፣ በተከታዩ የዓለማቀፍ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ በክብር እንግድነት ይጋበዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትናንት እና ዛሬ በአማራ ክልል ከ20 በሚበልጡ እና በሌሎች የተለያዩ ከተሞች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጅምር የለውጥ እርምጃ በመደገፍ ታላላቅ ሰልፎች ተካሂደዋል።በሰልፎቹ የዶክተር አብይ፣ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአቶ ለማ መገርሳ፣ የአቶ ደመቀ መኮንን ከተቃዋሚዎችና ከጋዜጠኞች ደግሞ የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የአርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በዬነ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የሎሎች አክቲቪስቶች ምስሎች ደምቀው ታይተዋል።

ከተሰሙት መፈክሮች መካከልም፦”ለውጡን ለማደናቀፍ የምታሴሩ አርፋችሁ ተቀርመጡ! ለማ መገርሳ የቄሮ ንስር!” የሚሉትና ሌሎችም ይገኙበታል። በባለፈው ጥምቀት በአጋዚዎች ክፉኛ የተጨፈጨፉት የወልድያ ወጣቶች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፎቶ በትልቁ ይዘው በመውጣት ከሥሩ ባሰፈሩት ጽሁፍ ፦” ዶክተር አብይ፣ የወደድንህ ስላልሞትን፣አይደለም፣ የወደድንህ ስላልታሰርን አይደለም።

የወደድንህ ከኛ ብሄር ስለሆንክና ስላልሆንክ አይደለም። የወደድንህ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ስለወደድክልን ብቻ ነው” ማለታቸው የብዙዎችን ስሜት ነክቷል።

እነዚህንና ሌሎችን መረጃዎች አጠናቅረናል።
ትንሳኤ- የእርስዎ ራዲዮ!

No comments