“የአዲስ አበባ ጥያቄ የማንነት እንጂ የከተማ አይደለም”
“የአዲስ አበባ ጥያቄ የማንነት እንጂ የከተማ አይደለም” በማለታቸው የተነሳባቸውን ሕዝባዊ ተቃውሞ በተመለከተ የተጠየቁት ከንቲባ ታከለ ኩማ፦ ''በወቅቱ የሰጠሁት አስተያየት በተለየ መልኩ መተርጎም የለበትም። የስጋት ምንጭም መሆን የለበትም'።አዲስ አበባ ብቻ ሳትሆን የትኛውም ከተማ ደሃውን ህብረተሰብ መግፋት የለበትምና''ብለዋል።
“አሁንም ቢሆን ''ጥቂት ግለሰቦች የአርሶ አደሩ መሬት ላይ ባለጸጋ ሆነው አርሶ አደሩንና የአርሶ አደሩ ልጅ ጥበቃ እና የጉልበት ሰራተኛ ሆኖ ማየት አልፈልግም” ያሉት ከንቲባ ታከለ፣ “ ይህ ደግሞ ኦሮሞን ብቻ የሚመለከት ብቻ ሳይሆን በከተማዋ እና በዙሪያዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሚመለከት ነው'' ብለዋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባንጸባረቋቸው ኢትዮጵያዊ አመለካከቶች እና ባለፉት ሦስት ወራት በወሰዷቸው በጎ እርምጃዎች ከዳር እስከ ዳር ከፍተኛ ሕዝባዊ ድጋፍ ያገኙት ዶክተር አብይ፣ በተለይ በሹመት አሰጣጥ ዙሪያ እየተነሳባቸው ያሉትን ቅሬታዎች ወደ ሌላ አዝማሚያ ከመለወጣቸው በፊት እርምት እንዲወስዱ ወይም ምላሽ እንዲሰጡ ደጋፊዎቻቸው ጭምር መጠየቃቸውን ቀጥለዋል።
-- በመቀሌው ስብሰባ የትግራይ ሕዝብ በኢፈርት ሀብት ውስጥ የአክስዮን ድርሻ ይኑረው በማለት በዶክተር ደብረጽዮን ቡድን የቀረበን ሀሳብ በመቃወም አቶ ስብሀት ነጋ ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸው እያነጋገረ ነው።
አቶ ስብሀት ፦”የትግራይ ሕዝብ በኢፈርት ውስጥ አምስት ሳንቲም ድርሻ የለውም። ሀብቱ የህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው።እኔ ጋር በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አለ።አላስረክባችሁም”በማለት ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን አቶ አስገደ ገብረሥላሴ ገልጸዋል።
አቶ ስብሀት ፦”የትግራይ ሕዝብ በኢፈርት ውስጥ አምስት ሳንቲም ድርሻ የለውም። ሀብቱ የህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው።እኔ ጋር በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አለ።አላስረክባችሁም”በማለት ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን አቶ አስገደ ገብረሥላሴ ገልጸዋል።
--በባሌ-ጎባ የቀይ ቀበሮው ሀውልት ለመፍረሱ እና ረብሻ ለመቀስቀሱ የአካባቢው መስተዳደር አካላት ከግጭቱ ጀርባ እጃቸው እንዳለበት ተመልክቷል። በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በቄሮ ስም የሚፈጸሙ ስርዓት አልበኝነት አሣሳቢ ደረጃ ላይ የደረሱ ሢሆን፤ እነዚህን ድርጊቶች ለእውነተኛ ፍትህ የታገሉ ቄሮዎች ራሳቸው እንዲታገሏቸው በርካቶች እያሣሰቡ ነው።
አቶ ለማ መገርሳ ሰሞኑን ፦”ጭቆናን መሸከም አንችልም ብለን ታገልን። አሁን እያሣሰበኝ የመጣው ነጻነትንስ መሸከም እንችላለን ወይ?”የሚለው ጉዳይ ነው ማለታቸው ይታወሳል።
-በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል እርቅና ሰላም መፈጠሩን ተከትሎ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች እየተሻሻሉ በመጡበት በአሁኑ ወቅት በሁኔታው የተደሰቱ የትግራይ ወጣቶች ደስታቸውን ለመግለጽ በእግራቸው ኤርትራ ደርሰው ሲመለሱ በትግራይ ፖሊስ ታሰሩ።
ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ እውነተኛ ሰላም መምጣታቸው እየተነገረ ባለበት እና ከአዲስ አበባ አስመራ በረራ የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚቀጥለው ሳምንት ከመቀሌ አስመራ እንደሚጀምር ባሳወቀበት ማግስት፣ ወጣቶቹ ኤርትራ ደርሰው በመመለሳቸው መታሰራቸው የትግራይ ክልል አስተዳደር ለእርቁና ሰላሙ ገና ልቡን ክፍት እንዳላደረገ የሚያመላክት ነው ተብሏል።
ሌሎችንም መረጃዎች አጠናቅረን ይዘን ቀርበናል።
ትንሳኤ -የእርስዎ ራዲዮ!
No comments