Latest

ትላንትና ዛሬ ጅግጅጋ ውስጥ ምንድነው የተፈጠረው? ስዩም ተሾመ

ጅግጅጋ ውስጥ ምንድነው የተፈጠረው?

ይህ ቅን ሰው በቴሌቪዥን ቀርቦ በሶማሌ ክልል አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን በተናገረ ሶስት ቀናት ውስጥ በጅግጅጋ ከተማ ሁከትና ብጥብጥ ተቀሰቀሰ፡፡ በዚህ ምክንያት በትላንትናው እለት የሁለት ሰዎች ህይወት ጠፋ፡፡  


ዛሬ ጠዋት በጅግጅጋ ከተማ የሚገኙ የንግድ ቤቶች በከፊል ዝግ ነበሩ፡፡ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ከቀብር መልስ ረብሻና ግርግር ተነስቶ ነበር፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ የጥይት ተኩስ እየሰሙ እንደሆነ ነግረውኛል፡፡ በአጠቃላይ ትላንትና ዛሬ በጅግጅጋ እየሆነ ያለው ነገር ከላይ ከተጠቀሰው የክልሉ ፕረዜዳንት ንግግር ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡

በህወሓት መሪነት የተዘረጋው የአፓርታይድ ስርዓት እድሜውን ለማራዘም የቀየሳቸው ስልቶች፤  

አንደኛ፦ ኢትዮጵያን በብሔር መከፋፈል እና ጎጠኝነት ገዢ የፖለቲካ አመለካከት እንዲሆን ማድረግ ነው፣ ሁለተኛ፦ በተለይ የሶማሌ ክልልን የሁከትና ብጥብጥ ቀጠና በማድረግ ፀረ-አፓርታይድ ትግሉን ማኮላሸት ነው፡፡ 

እንደ አብዲ ኢሌ ያለ የአዕምሮ መታወክ ያለበት ሰውዬ የአንድ ክልል ፕረዜዳንት ሆኖ የተሾመበት ምክንያት ለዚሁ ዓላማ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ተፈናቀሉ፣ ሺህዎች ደግሞ ለሞት ተዳረጉ፡፡

በመጨረሻ አብዲ ኢሌ እና ግብረ-አበሮቹ ታሰሩ፡፡ በምትኩ ጎጠኝነትን አምርሮ የሚጠየፍ፣ በአብሮነትና አንድነት የሚያምንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የነበረ ግለሰብ የክልሉ ፕረዜዳንት ሆነ፡፡ ይህን ተከትሎ በክልሉ ሰላም ሰፈነ፡፡

ፕ/ት ሙስጠፋ ይህን በይፋ ሲናገር በሌላ በኩል የሶማሌ ክልልን የሁከትና ብጥብጥ ቀጠና ለማድረግ የሚሹት ወገኖች ሽንፈትና ውድቀት እንደሚሰማቸው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ለዚህ እኩይ ዓላማ የተዘረጋው ኔትዎርክ እንደሆነ ሙሉ በሙሉ አልፈረሰም፡፡ ከላይ የነበረው አመራር እንጂ ከታች የነበረው አሁንም ባለበት ነው፡፡  

ስለዚህ እነዚህ ሽንፈታቸውን መቀበል ያቃታቸው የአፓርታይድ አቀንቃኞች ለሁከትና ብጥብጥ ዓላማ የሚውል የተወሰነ ፋይናንስ ይመድባሉ፡፡ በመቀጠል አብዲ ኢሌ ለዚሁ ያደራጃቸው ወጣቶች እና የተወሰኑ የልዩ ፖሊስ አባላት እንዲደርስ ማድረግ ነው፡፡ 

ገንዘቡ በአብዲ ኢሌ እናት በኩል ከአዲስ አበባ ይላካል፣ ጅግጅጋ ላይ ልዩ ፖሊሶች ሁለት ሰዎችን ይገድላሉ፡፡ ዛሬ ደግሞ በጠዋት መጠጥ ሲጠጡ ከቆዩ በኋላ ከቀብር መልስ ብጥብጥ ያስነሳሉ!! 

ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ነገሮች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲቀመጥ ግን እውነታ ይኸው ነው!!

No comments