የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 4 [ከአስጌ]
ደግሞ ሌላ ነው ስትባይ ስለ ፍቅር እሚያወራ መፅሀፍ ለመፈለግ እንዳትደክሚ መፅሀፉ { መምፈሳዊ } መፅሀፍ ነው። የምርህ ነው አለች መገመት ያልቻለችው ጓደኛየ። አወ የምሬን ነው። ለዛም ነው የገረመኝ። እርእሱ ነገረ ማርያም} ይላል።
የመፅሀፉን ግርባብ ገለጥ ሳደርገው የመጀመርያው ገፅ ላይ ከሜሮን ለናትናኤል ይላል በጥቁር እስኪብሪቶ የተፃፈው ፅሁፍ። መፅሀፌን ለማንበብ ግን ሰአት ስለሚወስድብኝ የተሰጠኝን ስጦታ ወደ ፖርሳየ መልሼ የተፃፈልኝን ደብዳቤ ወደ መፀዳጃ ቤት ልጥል ተሰስቼ ከመኝታ ክፍሌ ስወጣ ምሳ አትበላ አለች ታናሽ እህቴ እኔም አስከተልኩና መጣው መፀዳጃ ቤት ነኝ አልኩና ያንን ደብዳቤ ይዤ መፀዳጃ ቤት ገባው።
እናጣልከው ለማንም ሳታሳይ አለች ያች ታሪክ ሰሚዋ ጓደኛየ። አልጣልከትም ግራ ተጋባውና አስቀመጥኩት መልሼ። እሽ ከዛስ ከዛማ ያው ተመለስኩና ተጣጥቤ ምሳየን ልበላ ተቀመጥኩኝ። ግን እኮ የምፈቀርና የምወደድ ልጅ አይደለሁም።
ማለት አለች ታሪኬን እንደ መፅሀፍ ልታነብ የጓጓችው አድማጬ። ማለትማ በቃ እኔ እንደሌሎች የሀብታም ልጅ አይደለሁም ደግሜም እኔ ዘመናዊ ወጣት አይደለሁም። ዘመናዊ ነገርም አይመቸኝም። እንዴት እኔን ልታፈቅረኝ ትችላለች በሚል የሀሳብ አሩንቃ ውስጥ እንደተዘፈኩ ምሳየን የበላውበትን እቃ የምታጣጥብልን እህቴ መጥታ ስታነሳው ነበር የነቃውት።
ምሳየን የበላውበትንና ሌሎች እቃወችን ጨምራ ለማጣጠብ ሰብስባ የምትወጣውን እህቴን ተከትየ ከቤት ወጣውና ወደ ነበርኩበት የመኝታ ክፍሌ አመራሁ። ገብቼም የተሰጠኝን መፅሀፍ ማገላበት ጀመርኩ። መፅሀፉን ለስሙ ነው እንጅ እማገላብጠው አንድም ነገር ማንበብ አልቻልኩም። ሀሳቤም ትካዜየም ሙሉ በሙሉ ስለ ማሮን ደብዳቤ ሆነ።
ደብዳቤው የውሸት እንደሆነ ብቻ ሆነ እማስበው። ስለደብዳቤው ምንም ጥሩ ነገር አልታይ አለኝ። ይሄንን ደብዳቤ ለማንም ሳላሳይ ላስቀምጠው ወሰንኩና ቃሌን ጠብቄ እማይገኝ ቦታ ውስጥ ደበኩት።
[ግን እኮ ሴትን ማመን አስረግዞ ነው] የተባለውን ንግግር መስማት በራሱ በሴት ልጅ ላይ ያለን እምነት እንደሚቀንስና እንደሚያጎድፍ አውቃለሁ።
.......እኔ ግን የጓደኛየን የመልካሙን ታሪክ በደምብ ስለማውቅና ሴት ልጅ አፍ አውጥታ ከጠየቀችህ ያች ልጅ #ጤነኛ አይደለችም። ወይም ደግሞ አንተ ሳትላቼው ወደ አንተ መቅረብ እሚፈልጉ ሴቶች ጤነኞች ስላልሆኑ እንዳትቀርባቼው።
ብሎ የነገረኝን የአባቴን ንግግር በመደጋገም አምሮየ ላይ አዳመጥኩ። የአባቴ የማስፈራርያ ንግግርም አምሮዬ ላይ ደጋግሞ ያቃጭልብኝ ጀመር። ንግግሩንም መርሳት አልቻልኩም። እና ምን ሆንክ አሽ ከዛስ አለች የተከሰተውን ነገር ለመስማት።
ከዛማ ያው ዝምታህ አሽ አንዳልክና በሀሳቤ እንደተስማማህ ነው እሚቆጠረው ስላለች እኔም እንዲህ በማለት መልሴን አስቀመጥኩላት። ምን አልካት አለች መልሴን ለመስማት የጓጓችው ይህችው ተሳፋሪ።
ኧረ ብታይ ስንቴ ፅፌ ስንቴ እንደሰረዝኩ ያ ብቻ መስሎሽ ሰንት ወረቀት እንደቀደድኩና እንደፈጀው ብታይ ስል እንዴ ለምንህ አለች እኔ እንዲህ አይነት ነገር ፅፌ ስለማላቅ ነዋ ያው በመጨረሻ ግን ይህንን ፃፍኩላት። የቱን አለች ወረቀቱን ለማየት እያሰበች። አይ እኔ ላንብብልሽ አልኩና ከእርሴ ጀምሬ አነበንብላት ጀመር።
....................
ክፍል 5 ይቀጥላል
No comments