Latest

ታከለ ኡማ ያሰማራቸው ወጣቶች የአዲስ አበባን መሬት በወረራ እየተቀራመቱ ነው!



ታከለ ኡማ ያሰማራቸው

የታከለ ኡማን መመሪያ የያዙ ከከተማው ውጭ የመጡ ወጣቶች አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝን መሬትን በወረራ እየያዙ በመቀራመት ላይ መሆናቸውን ከአዲስ አበባ በውስጥ መስመር ከተላከ የታመነ ምንጭ ለማወቅ ችለናል።

ምንጫችን አያይዞ እንደገለጠው ተኝተው በተነሱ ቁጥር በየቀኑ አጠገባቸው ቤት ተሰርቶ እንደሚያኙና በጉዳዩ የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች ጭምር ግራ እንደተጋቡ ገልጿል።

ለምሳሌ በትናንትናው እለት ከከተንቲባው ጽሕፈት መመሪያ ወረቀት የያዙ፣በማንኛውም የአካባቢው ሰው የማይታወቁና ኦሮምኛ ብቻ በሚያወሩ ወጣቶች አየር ጤና አካባቢ በሚገኙ ክፍትና በፓርክነት በሚያግሉ ቦታዎች ላይ 175 ሜትር ካሬ እየለኩ መሬቱን ሲቀራመቱ መዋላቸውን ወጣቶቹ አጥረውት የሄዱበትን ቦታ በፎቶ ጭምር በማያያዝ ማስረጃ አድርሶናል።

ታከለ መሬት እንዲወሩ ያሰማራቸው የአዲስ አበባን መሬት በወረራ የሚቀራመቱ ወጣቶች ከአዲስ አበባ ውጭ መምጣታቸው ብቻ ሳይሆን ሕጋዊ የሆኑት የቀበሌና የክፍለ ከተማው ኃላፊዎች እንኳ «ለምን ታጥራላችሁ፤ ማን ፈቀደላችሁ» ቢሏቸው ምን አገባችሁ!  

በማለት በጉልበት ያገኙነት መሬቱ ሁሉ ማጠራቸውን መቀጠላቸውን፤ ፖሊሶች ተጠርተው ቢመጡም የተፈጠረውን እንግዳ ነገር አስመልክቶ አካባቢው ላይ ሰብሰብ ብለው ሲማከር የነበሩ የሰፈር ወጣቶች ሲያዋክቡና ሲመቱ እንጂ መሬት ወራሪዎችን ማስቆም እንዳልቻሉ ምንጫችን ገልጦልናል።  
በትናንትናው እለት አየር ጤና አከባቢ መሬት በወረራ እየያዙ በማጠርና በመከፋፈል ላይ የነበሩ ወጣቶች በዛሬ እለት ተመልሰው እንደሚመጡና በፓርኩ ውስጥ ያለውን ዛፍ እየቆረጡ የቀረውን መሬት እንደሚከፋፈሉ ተናግረው መሄዳቸውን የአየር ጤናው ምንጫችን በውስጥ መስመር ከአዲስ አበባ በላከው መልዕክት ገልጧል!

ከአቻምየለህ ታምሩ የፌስቡክ ገጽ የተገኘ

No comments