Latest

“የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለማደራጀት ተንቀሳቅሰዋል” ተብለው የታሰሩት ፍርድ ቤት ቀረቡ

(ከግራ ወደ ቀኝ) አቶ ሄኖክ አክሊሉ እና አቶ ሚካኤል መላክ።
(ከግራ ወደ ቀኝ) አቶ ሄኖክ አክሊሉ እና አቶ ሚካኤል መላክ።
ከዚህ ቀደም ህወሃት በሽብር ወንጀል ለሚከሳቸው አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች (አቶ ታዬ ደንደአን ጨምሮ) ጠበቃ በመቆም የሚታወቀው ወጣቱ የህግ ባለሞያ አቶ ሄኖክ አክሊሉ እና እንዲሁም አቶ ሚካኤል መላክ በትላንትናው እለት በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል።

ፖሊስ ዛሬ ግለሰቦቹን የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ያቀረበ ሲሆን “አዲስ አበባ በክፍለ ሀገር ልጆች አትመራም” በማለት “ከፍሊስጤም ኢምባሲ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የአዲስ አበባ ወጣቶችን በመቀስቀስ እና በማደራጀት ሲንቀሳቀሱ… ተይዘዋል” በማለት ወንጅሏቸዋል።

ፖሊስ ሌሎች ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እና ቀጣይ ምርመራ ለማካሄድ የ7 ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

በዋነኛነት ጠበቃ ዳማው አስፋውን ጨምሮ ስድስት ጠበቆች ለተከሳሾች ጥብቅና ቆመውላቸዋል።

ቀደም ሲል ህወሃቶች “አሸባሪ” የሚል ስም እየሰጡ የስልጣን ስጋት ያሳደሩ ተቃዋሚዎችን እና አክቲቪስቶችን እንደሚያስሩ ሁሉ የጠ/ሚ አብይ አህመድ አስተዳደርም ያንኑ አይነት መንገድ እየተከተለ ይመስላል።

ግለሰቦቹ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለማደራጀት በመንቀሳቀሳቸው ለእስር ተዳርገዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶች መደራጀት ለምን ስጋት እንደፈጠረና የአዲስ አበባ ወጣቶች የመደራጀት መብት ለምን ተለይቶ እንደተገፈፈ የተገለጸ ነገር የለም።

በተያያዘ ዜና ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በጅምላ ታፍሰው ለአንድ ወር ያህል ጊዜ በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ታስረው የቆዩ የአዲስ አበባ ወጣቶች መፈታታቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 


በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶቹ እንዲፈቱ ለሦስት ቀናት የቆየ የማኅበራዊ ድረገጽ ዘመቻ ሲያካሂዱ ሰንብተዋል።

No comments