የሃዋሳ ገበያ ቃጠሎ - ቪኦኤ
በሃዋሳ ከተማ ከትናንት በስቲያ መስከረም 29/2011 ዓ.ም ምሽት በተለምዶ አሮጌው ገበያ ተብሎ በሚጠራው ትልቁ የከተማው የገበያ ሥፍራ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ የነጋዴዎቹን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ማውደሙን ነዋሪዎች ገለፁ።
ነዋሪዎቹ የእሳት አደጋ ማጥፊያ በፍጥነት ቢደርስ ኖሮ ንብረቶቹ መታደግ ይቻል ነበር ብለዋል። ቃጠሎው ሆን ብሎ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ አላቸው።
የከተማው አስተዳደር በበኩሉ የቃጠሎውን መንስኤ እየመረመረ እንደሚገኝ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ከፍተኛ ንብረት በቃጠሎ እንደወደመባቸው የሚናገሩ ነዋሪ አነጋግረናል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)
No comments