Latest

በአርባምንጭ ኢትዮጵያዊነት ከፍ ብሎ ውሏል!!

በአርባምንጭ ኢትዮጵያዊነት ከፍ ብሎ ውሏል!!

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አካላት አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ የዞኑ አመራር አካላትና የከተማ ነዋሪ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃሁ ነጋ የግንባሩ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦን ጨምሮ የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች ጥቅምት 16/2011ዓ.ም አርባምንጭከተማ ሲገቡ የዞኑ አመራር አካላትና የከተማዉ ነዋሪ ከአየር ማረፊያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል፡፡

የግንባሩ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተደረገላቸዉ አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀዉ ለዚህም የከተማዉን ህዝብ እና የዞኑን አስተዳደር አመስግነዋል፡፡

በዛሬው እለት በአርባ ምንጭ ኢትዬጵያዊነት ከፍ ብሎ ውሏል። ቄጤማ ይዘው ቁጣ የሚያበርዱ የአገር ሽማግሌዎች ያሉባትን አገር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ጎብኝተዋታል። ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የአገር ፍቅሩን የገለፀበት መንገድ አጃኢብ ነው

በተካሄደው ደማቅ ዝግጅት ላይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ካደረጉት ንግግር
"አርባምንጭ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ሆና በመልካም አስተዳደር እጦት ወደ ኃላ የቀረች ከተማ ናት"

"ጋሽ አሠፋ ጫቦ ዛሬ አብረውን በመንፈስ ከእኛ ጋር አሉ"
"የአርባምንጭ ታጋዮች በኤርትራ በነበሩበት ወቅት ሁሌም ሀሳባቸው የነበረው የጋሞ ጎፋን ህዝብ እንደ አማራ እና ኦሮሞ ህዝብ ለመብቱ የሚታገል ማድረግ ነበር"

"ጋሞ ለራሱ ሳይለብስ ሌላውን የሚያለብስ ጥበብ ሠሪ ነው"
"አርባምንጭ በግንቦት ሰባት ትልቅ ቦታ አላት"

"የአርባምንጭ ታሪክ በግንቦት 7 ይቀየራል"


"ዛሬ እናንተ ፊት የቆምኩት ጀግኖች የአርባምንጭና የኢትዮጵያ ልጆች በከፈሉት መስዋዕትነት መሆኑን ለሰከንድ እንኳ የምዘነጋው ነገር አይደለም"
"ከዚህ በኋላ ሰው በሀገሩ ላይ ጥሮ ግሮ ሰርቶ እንዲከብር እንጂ ከመንግስት ጋር እየተሞዳሞደና መሬት እየሸጠ እንዲከብር አንፈቅድም"
ዘረኝነት ይወድማል !!!
ኢትዮጵያዊነት ይለመልማል !!!

No comments