መታወቂያ አሰጣጥን በዘመናዊ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረገ ነው - አስተዳደሩ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪነት መታወቂያ አሰጣጥ በዘመናዊ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጀነር ታከለ ኡማ እንደገለፁት ከዚህ በፊት በተለያዩ የመንግስት የልማት ስራዎችን ለማስፈፀም በነዋሪነት መታወቂያ ምክንያት አድሏዊ አሠራር እንደነበረም ገልፀዋል፡፡
ይህንንም አሰራር ለማሻሻል እና በከተማ አስተዳደሩ ፍትሃዊ የመንግስት አገልግሎት ነዋሪዎች እንዲያገኙ ለማስቻል በማሰብ የነዋሪዎች መታወቂያ መዘጋጀቱ ገልፀዋል፡፡
የነዋሪዎች አሻራ በመረጃ ቋት ስለሚካተት የመታወቂያ ድግግሞሽን በማስቀረት አንድ ሰው አንድ መታወቂያ ብቻ እንዲኖረው ይደረጋል ብለዋል፡፡
በሀብታሙ ደባሱ
No comments