Latest

"የአባቶቸን ርስት አልሰጥህም" (የነውር ጥግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ) [መስቀሉ አየለ]



የነውር ጥግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ

የሰው ልጅ ታሪክ የጀመረው ከእኛ ነው ስንል አፈታሪክ አይደለም። ፈረንጅ ቆፍሮ ያወጣት ሉሲ የሄዋን አጽም አለመሆኑን ማስረገጥ ከባድ ነው።
 


ከዚህ ስንነሳ ዛሬም ድረስ በእኛ አገር የሰምጥ ሸለቆ ዳርቻዎች አጽመ ቅሪቱን ፍለጋ ነጮች የሚያቀላጥፉት የአዳምን አለመሆኑን መሞገት አይቻልም። በዚህ ጉዳይ የሰው ዘር ታሪክ የጀመረው ከእኛ መሬት ላይ ነው ብሎ ትከሻውን ከእኛ ጋር ሊለካ አጠገባችን የቆመ አውሮፓዊ የለም።


ከኪዳነ አዳም እስከ ኪዳነ ኖህ፣ ከኪዳነ ኖህ እስከ ኪዳነ አብራሃም፣ ከኪዳነ አብራሃም እስከ ኪዳነ ሙሴ፣ ከኪዳነ ሙሴ እስከ ሃዲስ ኪዳን በእኛ ውስጥ አሻራውን ያላኖረ ኪዳን የለም፤ ስለሆነም ህገ ልቦናን ከብሉይ ፣ ብሉይን ከሃዲስ ለማስማማታችን መሰረቱ ይሄው ነው። 


በዚህም የተነሳ የሚበላውን ከማይበላው ገና በጠዋቱ ልይተን፣ እምነትን በግርዘት አጽንተን እምነትን ከምግባር፣ ዶግማን ከቀኖና ያስታረቅን የመልከጸዴቅ ልጆች ነን። የሞራልም ይሁን የባህል እንዲሁም የስነልቦናችን መሰረቱ ይኼው ነው።


የቀን ጅቡ ግን አንድ ብሎ እግሩን ወደ መሃል አገር ሲያስገባ እንደ ብልጣሶር እጁን ወደ ቤተመቅደሱና ወደ መሰዊያው የሰደደው የተላከበትም የተፈጠረተበትም ቢሆን ነው።

ለንጽጽር የጥቂት አገሮችን ተሞክሮ እንመልከት

በ፪ኛው የአለም ጦርነት ስታሊን ግራድ ላይ ያውም በበረዶ መካከል ተሰንቅሮ በቀዩ ጦር ለወራት የተከበበው የናዚ እግረኛ ጦር ከደረሰበት እረሃብ ለመትረፍ ወታደሮቹ እርስ በርሳቸው መበላላታቸውን ከዚያ እልቂት የተረፉት በናሽናል ጆግራፊ ዶክሜንታሪ ላይ ቀርበው ሲናገሩ ባይናችን ብሌን አይተናል።


የቀድሞው የሶቮየት ኤምፓየር መሪ ስታሊን በዩክሬን ገበሬዎች ላይ በወሰደው እርምጃ አገሪቱ ውስጥ እህል የሚያመርት ገበሬ በመጥፋቱ መሃል ከተማዋ ኬቭ ላይ ዩክሬናውያን መበላላት በመጀመራቸው በወቅቱ የነበረው የዩክሬን መንግስት "ሰውን መብላት ነውር ነው" የሚል መፈከር በዋና ዋና የኬይቭ አውራጎዳናዎች ላይ ሰቅሎ እንደነበር ካሜራ ለዛሬው ትዝብት መዝግቦታል።


ከ1958 -1961 ቻይና ውስጥ በደረሰው አሰቃቂ ረሃብ ወደ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ሲያልቅ ከዚህ ውስጥ ከፊሉ የሞተው ረሃቡን መቋቋም ባቃታቸው ቻይናውያን ተበልቶ እንደነበር እራሳቸው እነ ማኦ ዜዱንክ አልካዱትም።
 


ቻይና እስካቬንጀር ለመሆን ቢፈልግ እንደኛ የሚያቆመው ከአርያም የወረደ የሞራል ህግ ባይኖረው ነውና ዛሬ ያ የቻይናውያን ድኩማን ተፈጥሮ ጸያፍ በሆነው የአመጋገብ ባህላቸው አውሬ ሆኖ ተፈጥሮ የሚተውት ነገር ባለመኖሩ ቢገለጥ የሚገርመው የለም።

የበረራ ቁጥር 571 የዩራጋይ አውሮፕላን አርባ አምስት መንገዶችን ይዞ 1972 በረዶ ውስጥ በመከስከሱ አርባ አምስት ያህል ተሳጋሪዎችን ይዞ ቢጠፋም ከዚህ መካከል አስራ ስድስት ያህሉ ብቻ ተርፈው ከሰባ ሁለት ቀን ቦሃላ ለመገኘት የቻሉት የሌሎቹን ተሳፋሪዎች አስከሬን ሲመገቡ በመቆየት ነበር።


ቦብ ጊልዶፍ የፈረንጆችን ሚሊኒየም አስመልክቶ በሰራው ዲክሜንተሪ ላይ አፍሪካን ከላይ እስከታች ለማካለል የሞከረ ሲሆን ሴራሊዪን ገጠር ውስጥ የሚገኙ ጎሳዎች ከመካከላቸው አንዱ ከታመመና የማይድን ከመሰላቸው ሰውየው ሳይሞት ቀድመው የሚበሉት የቅርብ ጓደኞቹ መሆናቸውን ታዝቦ ነበር።
 


"ለምን?" ሲባሉ ግን መልሳቸው "ስለምንወደው አፈር ከሚበላው ብለን ነው" የሚል ነው። ይህ ሰው ከታች ከደቡብ አፍሪካ የጀመረውን አፍሪካን የማካለል ጉዞ ኢትዮጵያ ላይ ሲጨርስ ጉዞውን የደመደምው እንዱህ በሚል መሪ ቃል ነበር። "እኔ ..." አለ ቦብ ጉዶልፍ፤ "እኔ እንደገና የመወለድ እድል ቢገጥመኝ መወለድ የምፈልገው ኢትዮጵያ ውስጥ ነበር" ።


ባንድ ወቅት በዚህ ገጽ ላይ በሰፊው እንዳስነበብኩት የጉጅሌው ጭፍሮች አርማጮሆ ላይ በደርግ ጦር ተከበው ለቀናት ዋሻ ውስጥ ያለ ምግብና ውሃ ከከረሙ ቦሃላ መጨረሻ ላይ ሲማረኩ እርስ በርሳቸው ተበላልተው ተርፈው የተገኙት ግማሾቹ ብቻ እንደነበር ምንጭ ጠቅሻለሁ።

ይህ አይነት ወደ አውሬነት የወረደ ልማድ አንዲት አገር ውስጥ የከፋ የረሃብ ዘመን ስለተከሰተ ብቻ ሊፈጸም የሚችል ክስተት ነው ብለን እንዳንደመድም ዛሬም ድረስ እንደ ጀርመን ባሉ ባለ ጸጋ አገራት አካባቢ አልፎ አልፎ በሚዲይው የሚሰማው ነገር የሰው ጆሮ ቀርቶ የጭነት አህያ የሚችለው አይመስልም።
 


ለምሳሌ ከጥቂት አመታት በፊ እኔን የሚበላኝ ሰው እፈልጋለሁ ብሎ ማስታወቂያ የለጠፈን የዞረበት ሰው ጀርመን ውስጥ አንድ ፈቃደኛ ተገኝቶ በማይክሮዌቭ ጠብሶ እንደበላው የጀርመን ፖሊስ አስታውቆ ነበር።

ከዚሁ የምእራብ አፍሪካ አገራት ሳንወጣ በዚሁ አካባቢ ያሉትን እንደ ኮንጎና ሴኔጋል የመሳሰሉትን አገሮች ብናይ በጫካ ውሥጥ የሚኖርና ስጋ የለበሰ እስከሆነ ድረስ ተጠይፈው የሚተውት ምንም አይነት የዱሬ አውሬ የለም።


ይልቁንም ከጥቂት አመታት በፊት ይህንን የአህጉሩን ክፍል የመታው የኢቦላ ቫይረስ ዋነኛ ምንጩ የዚህ አካባቢ ተወላጆች በከፍተኛ ሁኔታ የሌሊት ወፍ ተመጋቢ በመሆናቸው እንደነበር በወቅቱ የተባበሩት መንግስታት የጤና ማእከል ማስታወቁን አስታውሳለሁ።

ስመ ጥሩው የነገረ መልኮት ሊቅ አቡነ ታድሮስ ማላቲ ክራይስት ኢን ዘ ዩካሬስት በሚለው መጻሃፋቸው ላይ Feuebrach ስለተባለ ጀርመናዊ ማቴሪያሊስት ፈላስፋ የጠቀሱት ነገር አለ። ይህ ፈላስፋ ሰውን ከሰብእናው ሲያወርደው "የሰው ልጅ ማንነት የሚወሰነው በሚበላው ነገር ነው" ማለቱን ይጠቅሳሉ።


ዛሬ ወደዚህ አርእስተ ጉዳይ የጎተተኝ ምክንያት ወዳጀ አርበኛ ፊደል ዳንኤል ከኮምቦልቻ ወደ አዲስ አበባ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET 167 ባደረገው የአገር ውስጥ በረራ የገጠመው አሳዛኝ መስተንግዶ ሲሆን ይኼውም በአባሪው ፎቶ ላይ የምታዩትን ትላትል አስተናጋጇ ፊቱ ላይ ቁጭ ስታደርግለት "ባይኔ ነው ወይንስ በቴለቪዥን " ማለቱ ነበር።

እነ አንበጣና በለስ ትናንት አዲስ አበባ አፍንጫ ስር የአህያ ቄራ ሲያቆሙ ሰምተን ያነባነው ለሽዎች አመታት ከማተባችን ጋር ቁዋጠርን ያቆየነው ሰማያዊ ትውፊታችን መና ቀረ ብለን ነው።


እነሱ አንበጣ በልተው ስለኖሩ እኛን ደግሞ የሰው አገር ቅንቡርስ በማስበላት ከወረዱበት ሊያወርዱን፤ ከሰውነት አውጥተው ከጉግማንጉግ ተራ ሊያቆሙን መሆኑ ስለገባን ነው። 



ዛሬ አየር መንገዱ እንዲህ አይነት ጽያፍና ያልተለመደ የሰው አገር ምናምንቴ ያውም በአገር ውሥጥ የበረራ አገልግሎት ሲያቀርብልን አላማውም ሆነ ሂደቱን ወደዚህ የገፋው ተጨባጭ ምክንያት ምን እንደሆነ እስከዛሬ ድረስ ለምን ከሰው ተሰውሮ እንደከረመ ግልጽ አይደለም።

No comments