Latest

አቋም! ብሄራዊ አርማ ይከበር! የድርጅት እና የሀገር አርማ ይለይ - እስማኤል ዳዎድ እንድሪስ

አቋም! ብሄራዊ አርማ ይከበር

ሕዝብ የፈለገውን አርማና ምልክት ለሕዝብ ሞራል እና ለህግ ባዳ ወይም ተቃራኒ ለምሳሌ  የጌ ራይትስ እና የአለም አቀፍ ስምምነት ዉስጥ ስማቸው በዐለም አቀፍ የተካተቱ በሽብር ወንጀል የሚጠረጠሩ ድርጅቶች እስካልሆነ ድረስ ይዞ መውጣት ይችላል ።

1ኛ በሕዝብ በግለሠቦች እና አካባቢ ማሕበረሰብ የተሠሩ መንገድ፤ አደባባይ፤ አጥርና ሕንፃ የተለያዩ ተቋማት፥ በማይለቅ ቀለም (ለማፅዳት ሲፈለግ) መቀባት ተቀባይነት የለውም። መልሶ ለማስለቀቅም ተጨማሪ ወጪና ጉልበት ይጠይቃል። ተጨማሪም የሕግ ተጠያቂነት ዉጪ ማንም እንዳሻው ይሆናል ስርዓት አልበኝነት ይሰፍናል፤ የግለሰቦችን ባለቤትነትና የይዞታ መብት ይጥሳል።

2ኛ በጨርቅ ላይ የተሠሩም ከሆነ የሱ እንዲነሳ እንደማይፈልገው የሌላውን እያነሱ የረጋዉን ሰላም ማደፍረስ፥ ውዝግብና የከተማ ነዉጥ መፋጠር፥ ሕዝቦችን ማወክ፥ በጋራ የመኖርን አስተሳሰብ የሚቃረን የቀን ጅቦች አመለካከት ነው።

3ኛ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ በኃላ ይህን መሠል ሁኔታዎች የሚሰተናገድበትን የህግ አግባብ መተግበር ወይንም መደንገግ የግድ ይለዋል!!

4ኛ ከዚህ ድርጊት ጀርባ ሁልጊዜም ያላችሁ በማስተር ኬ ሞተሩን አቀጣጥላችሁ የፓለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ አክቲቪስቶች የዚህ አይነት ፋክክር ለሐገርም ሆነ ለምታራምዱት አላማ አስተዋፆው ጠቃሚ ስለማይሆን አብሮ በመኖር እሳቤ ጉልበትንና አቅምን ለሀገር እንዲውል በመምከር በስሜት ያነደዳችሁዋቸዉን ወጣቶች ከዚህ አይነት ድርጊት እእንዲታቀቡና አቅል እንዲሰበስቡ መምከር የተሻለ ነው። "አብዛኛዎቻችሁ እንተዋወቃለን" !!

በዚህ መነፅር ካየነው ዘንዳ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት። ማንም የፈለገውን "ቆሌዉ ደስ የሚያሰኘውን" የመረጠዉን የመያዝ መብት አለው።

ማንም የተለየ ቅዱስ ደም ለዚህች ሀገር ያፈሰሰ የለም! ማንም !!! እደግመዋለሁ ማንም !!! ሁላችንም በአንድ ጉድጓድ የተቀበርን የዘረኛ አምባገነኖች ግፉአን ነን።

ከሁሉም ከሁሉም የሕግ ጉዳይ ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ ተብሎ የሚተዉ አይደለም "ማንም ኢትዮጵያዊ" ብሄራዊ አርማዉን ያከብራል !! ያስከብራልም !!

No comments