ቁጭ እሷን ባንዲራ! (አሌክስ አብርሃም)
ብሔር ሲባል <<ጥላቻ >> እና <<ፍቅር>> የሚል ንትርክ ውስጥ የሚገባ ሰው ይበዛል! ብሔረተኝነት ጥላቻ ላይ አይመሰረትም ፣ ብሔርተኝነት ፍቅርም ላይ አይመሰረትም ፣ ብሔርተኝነት ብልጣብልጥነት ላይ አይመሰረትም !
ብሔርተኝነት የሚመሰረተው ራሱ ብሔሩ በብሔርተኝነት ብቻ ሊፈታ የሚችል ችግር አለኝ ካለ ብቻ ነው!! ለማንኛውም የኔን አቋም ለምትጠይቁኝ ፣ ማንም ብሔር በብሔርተኝነት እደራጃለሁ ካለ መጠላትም መገፋትም መሰደብም መወገርም የለበትም !!
ማንም ተመኔ ኢትዮጲያዊነት ነው ካለም ማን ፈቅዶልህ ኢትዮጲያዊ ሆንክ መባል የለበትም ! በተለይ በማይረባ የስም ማጥፋትና ማጠልሸት ዘመቻ አንድን የፖለቲካ አመለካከት ፣አንድን እምነት፣ አንድን አካል በህዝብ ዘንድ ለማስጠላት መራዎጥ እልኽኛ ብሔርተኝነትን፣ አክራሪ ሃይማኖተኝነትንና ፣ ጽንፈኛ ቡድንን ይወልዳል !
የሰው ልጅ አገር ከማለቱ በፊት ብሔር ፣ ብሔር ከማለቱ በፊት የትውልድ ከተማ፣ ከዛም በፊት ሰፈሩን እንደሚወድ ምንም ጥርጥር የለውም ! እና ለምን ይመስልሃል <<መርካቶ ሰፈሬ >> ሲባል የመርካቶ ልጅ አንጀቱ የሚንሰፈሰፈው፡)
የሰው ልጅ አገር ከማለቱ በፊት ብሔር ፣ ብሔር ከማለቱ በፊት የትውልድ ከተማ፣ ከዛም በፊት ሰፈሩን እንደሚወድ ምንም ጥርጥር የለውም ! እና ለምን ይመስልሃል <<መርካቶ ሰፈሬ >> ሲባል የመርካቶ ልጅ አንጀቱ የሚንሰፈሰፈው፡)
ለምን ይመስልሃል አራት ኪሎ ፈርሶ ነዋሪው ምንትስ ኮንዶሚኒየም ግባ ሲባል ሱዳን ስደት የሄደ ያህል ሆድ የሚብሰው? አሮጌ ግርግዳው የሚያፈስ ጣራው ናፍቆት ነው? አይደለም !! የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ እንደሰፌድ የኑሮ ሰበዝ እየተጨመረበት ከነቁጥ ተነስቶ ከበቡ ይስፋል ፣ ጠጠር እንደወረወሩበት ውሃ ከመሃል ጀምሮ እየሰፋ ትልቅ ከብ ይሆናል !
ከአንድ ኢትዮጲያዊ የሚጠበቀው ሁሉንም ማክበር፣ ተቃውሞ ካለው በመንጋ ሳይሆን በስርዓት የሃሳብ ልዩነቱን ማቅረብ ብቻ ነው !!
ከአንድ ኢትዮጲያዊ የሚጠበቀው ሁሉንም ማክበር፣ ተቃውሞ ካለው በመንጋ ሳይሆን በስርዓት የሃሳብ ልዩነቱን ማቅረብ ብቻ ነው !!
እና ደግሞ አለመፈረጅ ! ስለአንድ እምነት ስትጽፍ ግርር ብሎ የዛ እምነት ምንትስ ነህ ! ስለአንድ ድርጅት ስትጽፍ ግርር ብሎ የዛ ድርጅት አባል ነህ !
ስለአንድ ብሔር ስትናገር ግርር በሎ ዘረኛ ነህ የሚል ሰው ባንዲራችንን ይዞ ባየው እንኳን ለዚህ ሰው የባንዲራው ትርጉም አረንጓዴው ጫት ፣ ቢጫው ጠጅ ቀዩ በጥላቻ ደም የለበሰ አይኑ ነው ! ቁጭ እሷን ባንዲራ !!
No comments