Latest

አሳዛኝ ዜና! ካማሽ ዞን ላይ ንፁሃን የይድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነዉ! [ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወ/ስላሴ]

ካማሽ ዞን

በካማሽ ዞን አምስት ወረዳዎች አሉ፡፡ ካማሽ፣ በሎ ጅጋንፎይ፣ ያሶ፣ አጋሎ ሜጢ እና ሲርባ አባይ የሚባሉ ሲሆኑ አራት ሚሆኑ የካማሽ ዞን አመራሮችና የፀጥታ ሃይሎችን ትላንት ኪንጊ ካማሺ የሚባል ቦታ ላይ ይገድሏቸዋል፡፡

ይህንን የሰሙ የጉሙዝ ብሄረሰቦች ቀይ የተባለዉን በቀስትና በመሳሪያ በመፍጀት ላይ ናቸዉ፡፡ ብዙዎች ከያሶ ወረዳ ተፈናቅለዋል፡፡

በሎ ጅጋንፎይ ላይ ዳግም ከፍተኛ እልቂት ለመፈፀም የሞት ጥላ አጥልቶባቸዋል፡፡ አጋሎ ሜጢ ወረዳ ቤታቸዉን ዘግተዉ በእህል ዉሃ የሚሰቃዩት በዝተዋል፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን የፌደራል መንግስት ዝምታን መርጧል፡፡ ንፁሃን የድረሱልን ጥሪ ከወደ ካማሽ እያሰሙ ነዉና ድረሱላቸዉ፡፡

የመንግስት የመሳሪያ ግምጃ ቤቶች እየተከፈቱ ከታዳጊ እስከ አዋቂ የጉሙዝ ብሄረሰብ መሳሪያ ታጥቋል፡፡ ከክላሽንኮቭ የማይተናነሰዉ ቀስቱን ይዞ በከተማዉ ዉስጥ የሚፏልለዉና ሰዉ የሚገድለዉ ጉሙዝ ብቻ ነዉ፡፡

የፀጥታ ሃይል እየገባ ነዉ እያሉ ተስፋ ይሰጡናል ግን እስከአሁን የደረሰ አንድም አካል የለም፡፡

No comments