Latest

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት ፈጸመ - ቢቢሲ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት ፈጸመ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ።

የምስራቅ ምድብ ሄሊኮፕተሮች ስኳድሮን አልሸባብ ላይ እርምጃ እንደወሰዱ አየር ኃይሉ ለኢቴቪ አስታውቋል።

የተዋጊ ሄሊኮፕተሮቹ ከደቡብ ምስራቅ እዝ እግርኛ ጦር ጋር ቅንጅት በመፍጠር አልሸባብ ላይ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል።

የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ ባካሄደው ኦፕሬሽን በአልሸባብ ላይ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ እና ሞራላዊ ውድመት አድርሰናል ሲሉ ለኢቴቪ ተናግረዋል።

አየር ኃይሉ የሃገሪቱን የአየር ክልል ከመቼውም በላይ በአስተማማኝ ሁኔታ ከመጠበቅ በተጨማሪ ለምድር ኃይሉ ድጋፍ በመስጠት በሃገሪቱ ላይ ሊቃጣ የሚችል ማንኛውም አይነት ወረራ እና የሽብር ድርጊት በአጭር ጊዜ ለመመከት የሚያስችል ጠንካራ ተቋም ነው ሲሉ ብርጋዴር ጀነራሉ ተናግረዋል።

ብርጋዴር ጀነራል ይልማ መርዳሳ በኦፕሬሽኑ ላይ የተሳተፉት የጦር ሥራዊት አባላትን አመስግነዋል።

No comments