Latest

ታላቁ ዲፕሎማት ኮፊ አናን ሲታወሱ

ታላቁ ዲፕሎማት ኮፊ አናን ሲታወሱ

(ቢቢሲ) - በ80 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ኮፊ አናን ለዘጠኝ አመታት ያህል በአለም ትልቁን አለም አቀፍ የዲፕሎማሲ አካል የተባበሩት መንግሥታትን መርተዋል።

በትልልቅ ክስተቶች በታጀበው እነዚህ አመታት በአሜሪካ ላይ 9/11 ተብሎ የሚታወቀው የሽብር ጥቃት እንዲሁም በአሜሪካ የሚመራው ጦር ኢራቅን ሲወር አመራር ላይ ነበሩ።

በተለይም በመጨረሻው የስልጣን ዘመናቸው ወቅት በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሰቃቂ የሚባሉ እንደ ሶሪያ የርስ በርስ ጦርነት ቀውሶችን ማስማማት የሳቸው ኃላፊነት ነበር።

በጄኔቫ የቢቢሲ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርተር ኢሞጅን ፎክስ ታላቁን ዲፕሎማት እንዲህ ታስታውሳቸዋለች።

በመፅሐፍ መደርደሪያየ ላይ "እኛ ህዝቦች፡ የተባበሩት መንግሥት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን " (ዊ ዘ ፒፕልስ ኦፍ ዩኤን ፎር ዘ ትዌንቲ ፈርስት ሴንቸሪ) የሚል መፅሐፍ አለ።

መፅሐፉ ኮፊ አናን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ በነበሩበት ወቅት በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች እንደ የአየር ፀባይ ለውጥ፣ ሰላም ማስከበር፣ ኤች አይ ቪ ኤድስና ዘር ጭፍጨፋን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ያደረጓቸውን ንግግሮች ስብስብ ነው።

ትልልቅ ችግሮችን ለመፍታት የመንግሥታት መማክርት አካል አስፈላጊነትን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላይ የሰላ ትችት የሚያቀርቡ አካላት በራሳቸው የተባበሩት መንግሥታት ባይኖር ኖሮ "እኛ መፍጠር እንደሚያስፈልገን" የሚያትቱ ፅሁፎችንም አካቷል።

ከዚህ ሁሉ በላይ ይህንን መፅሀፍ የምወደው ራሳቸው ኮፊ አናን ስለሰጡኝ ነው።

ከአራት አመት በፊት በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት መቀመጫ ዋና ፀሐፊነታቸው ሚና ላይ ያጠነጠነ ውይይትን ተሳትፈው ከወጡ በኋላ ነው የሰጡኝ።

በተባበሩት መንግሥታት መቀመጫ ጄኔቫ የተለያዩ ውይይቶች ይደረጋሉ፤ የሚመጡ ሰዎችም ቁጥር የሚያስከፋ አይደለም። በዛን ቀን ግን መቶዎችን የሚይዘው አዳራሽ ሞልቶ ብዙዎች ወደ አዳራሹ ለመግባት ውጭ ላይ ተሰልፈው ነበር።

ምንም እንኳን አንዳንድ ጨለምተኛ ሐሳብ ያላቸው ስለተባበሩት መንግሥታት መፅሀፍን ለማስተዋወቅ በዛው በተባበሩት መንግሥታት አዳራሽ ውስጥ ከማድረግ በላይ ሌላ ምን አለ የሚሉ አሉ።

ልክ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን የመፅሐፉ ሽያጭ ገቢ ሙሉ በሙሉ የተባበሩት መንግሥታት ኤችአይ ኤድስን ለመዋጋት በሚያደርገው ፕሮግራም እንዲውል ነው።

የዛን ቀንም የነበረው ውይይትም በዚሁ ላይ ያተኮረ ነበር።

መልካም ስብዕና
በአለማችን ላይ ተጋላጭ ለሆኑ ህዘቦች የሚያሳዩት የቸርነትና መንፈስና ፅናትን ብዙዎች ኮፊ አናን የሚያስታውሱበት ሁኔታ ይመስለኛል።

ዋና ፀሐፊም በነበሩበት ወቅት ከሳቸው በፊት ከነበሩም ሆነ ከሳቸው በኋላ ከነበሩ ኃላፊዎች በተለየ ወደ ጄኔቫ ይመላለሱ ነበር።

የፖለቲካው ተፅእኖም ሆነ ኃይል ተከማችቶ የሚገኘው በኒውዮርክ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጉዳዮች አለም አቀፍ ግጭቶችን ለመፍታት ክፍተት የሚታይበትም ለዚህ ነው።



ኮፊ አናን በተለየ መልኩ በጄኔቫ የሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶችን ድጋፍ መለገስና ትኩረት ያላገኙ ስራዎቻቸውንም ትኩረት እንዲያገኙ ማድረግንም ስራ ይሰሩ ነበር። በተቻላቸው መጠን ለሚዲያውም ጊዜ ይሰጡ ነበር።

ትህትናን የተሞሉና የጓደኛም ስሜትን የተሞሉ ናቸው። ጥያቄን በተአምር አይሸሹም ለምሳሌም ያህል ለተባበሩት መንግሥታት የሚዲያ አካል እንደተናገሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ ጥምር ኃይል የኢራቅን ወረራ ህገ-ወጥ ማለታቸው የሚታወስ ነው።

መልካም ስብእና ያላቸው ሰው ነበሩ። በአንዳንድ ወቅቶች መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት ተንበርክኬ ሲያዩኝ ፈገግ ብለው በኃዘኔታ ይመለከቱኝ ነበር።

በጄኔቫ የነበሩ ሁሉንም ጋዜጠኞችን ያስታውሳሉ፤ ሰው በጭራሽ አይረሱም ነበር። ለማውራት ጊዜ ባይኖራቸው እንኳን ቆም ብለው ሰው ሰላም ይሉ ነበር።

የሰላም ሻምፒዮን
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊነት ሚና በአለም ላይ ካሉ ፈታኝ የዲፕሎማሲያዊ ስራዎች አንዱ ነው።

ኮፊ አናን በኮሶቮ የነበረው ጦርነትን ለማስወገድ ትልቅ ሚናን የተጫወቱና የአየር ፀባይ ለውጥ ለአለም እንደ ስጋት የተደቀነውም በሳቸው ወቅት ነው።

የተባበሩት መንግሥታት በሳቸው አመራርም እያንዳዱን ችግርም አልቀረፈም።

በብዙ ተቺዎች ዘንድ በኮፊ አናን አመራር ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ስህተቶች ብለው የሚነቅሷቸው በሩዋንዳና በቦስኒያ የነበሩ የዘር ጭፍጨፋዎች፣ በኢራቅ የተከሰተውን ማዕቀብ ተከትሎም አንዳንድ ቢዝነሶችም የተባበሩት መንግሥታት ማዕቀቡን በማለስለሱ ነዳጅንም በመሸጥ የተፈጠረውን ቀውስ የመሳሰሉ ናቸው።

ከስህተቶቹ በተቃራኒ በጄኔቫ ኮፊ አናን የሚታወሱት በጦርነት ውስጥ ለሚማስኑና መሔጃ ላጡ፣ ለአካባቢ ቀውሶችና በድህነት ውስጥ ተዘፍቀው ላሉ ምላሽን በመስጠት አይረሴ አሻራን ጥለው አልፈዋል።



በተደጋጋሚም ለአለም መሪዎችን ምንም ያህል ኃይል ቢኖራቸውም ከፖለቲካ ጥቅም በፊት ዜጎቻቸውን ሊያስቀድሙ እንደሚገባ በአፅንኦት ይናገሩ ነበር።

ማረፋቸው ከተሰማ በኋላም በጄኔቫ የተለያዩ ኃላፊዎችም ታላቁን ዲፕሎማት እንዴት እንደሚያስታውሷቸው እየተናገሩም። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዘይድ ራኢድ ሑሴን "የሰብአዊነት መለኪያ" ብለዋቸዋል።

የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ዳይሬክተር ፒተር ማውረር በበኩላቸው ጥልቅ ኃዘናቸውን ገልፀው " ታላቅ ሰብአዊ መሪና የሰላም ሻምፒዮን" ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

የሳቸው ህልፈተ ህይወት በመላው አለም በተለይም በጄኔቫ ጥልቅ ኃዘንን ጥሎ ያለፈ ቢሆንም በጄኔቫ በተለይ ጓደኛችንን አጥተናል።

No comments