Latest

ኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኗን የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

 የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር

የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ በፅ/ቤታቸው በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ኢትዮጵያ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ ስራዎች የተከናወኑበት ነው፡፡


ሀገሪቱ በ2010 ዓ.ም ከጎረቤት ፣ከመካከለኛው ምስረቅ እና ከኤስያ ሀገራት ጋር የነበራት ግንኙት በመሪዎች የተደረጉ ግንኙነቶች ፍሬያማ እንደነበሩ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

ለ2 አስርት ዓመታት ሻክሮ የነበረው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙኑነት ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል በመስማማቷ ወደ ሰላም እና ወንድማማችነት መመለሱ በአብነት አንስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ጎረቤት እና መካከለኛው ምስረቅ ሀገራት በመሄድ ዜጎችን ማስፈታት መቻላቸው፣ከጎረቤት ሀገራት በወደብ እና በሌሎችም ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች መስማማት መቻላቸው ሌላው ስኬታማ ስራ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የዉጭ ጉዳይና ብሄራዊ የደህንነት ፖሊሲዋን መሰረት በማድረግ የራሷን የቤት ስራ መስራት በመቻሏ በጎረቤት ሀገራት ላሉ ችግሮች ከኢጋድ አባል አገራት ጋር በጋራ መፍትሄ በማፈላለግ ሚናዋ እየጨመረ መሆኑንም ገልፃል፡፡

በደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች የነበረው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲገኝ የራሷን ሚና መጫወቷን የገለፁት አቀባይ አቀባዩ አቶ መለስ፣ በጅቡቲና በኤርትራ መካከልም ከድንበር ጋር በተያያዘ ያለዉን ልዩነት በዉይይት እንዲፈታ የማደራደር ጥያቄ ማቅረቧንም አስታወሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እና በአባይ ወንዝ አጠቃቃም ዙሪያ ከሱዳን እና ከግብፅ መሪዎች ጋር ያላት ግንኙነት ከግድቡ በላይ የታሪክ ግንኙት እና ትስስር እንዳላት ማግባባት መቻሏ በድፕሎማሲ መስክ በዓመቱ የተመዘገበ ድል ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ለዓመታት እንደጠላት ይታይ የነበረው ዳያስፖራ (ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን) በሀገሪቱ ያለዉን የለውጥ ጅማሮ ለማስቀጠል የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ለመደገፍ እንቅስቃሴ መጀመሩ ትልቅ ስኬት አንደነበርም ተገልጿል፡፡

አሁን በሀገሪቱ እየተፈጠረ ያለው አንፃራዊ ሰላም፤የዳያስፖራ ተሳትፎ መነሳሳት፤መንግስት በህዝቡ ዘንድ ያለዉ ተቀባይት በመጠቀም በ2011ም የድፕሎማሲው ስራዎች ስኬት ለማስቀጠል ተከታታይ ተግባራት እንደሚሰሩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳምንታዊ መግለጫው አመልክቷል፡፡

በነቢል በቀለ

No comments