ብአዴን አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ከማዕከላዊ አባልነት አገደ
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አገደ።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ሁለቱን ነባር አመራሮች ያገደው መስከረም ወር እስከ ሚካሄደው ጉባዔ ድረስ ነው።
አመራሮቹ የታገዱት ጥረት ኮርፖሬት ውስጥ በፈፀሙት ችግር ነው ተብሏል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት ያደረገውን ስብሰባ ያጠናቀቀ ሲሆን በነገው ዕለት መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ለወራት በለውጥ ፈላጊ የብአዴን አመራሮችና የቆየውን አካሄድ ማስቀጠል በሚፈልጉ አመራሮች መካከል የተነሳው ልዩነት በድርጅቶች ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ተጽዕኖ የፈጥራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የመጀመሪያው ቀን ስብሰባ ያለ ምንም ችግር መጠናቀቁን ምንጮች ገልጸዋል።
ለውጡን የሚመሩት ሃይሎች ያቀረቡዋቸው አጀንዳዎች ያለምንም ችግር መጽደቃቻውን የገለጹት ምንጮች፣ አብዛኞቹ የጸደቁት አጀንዳዎች፣ ብአዴን እስከዛሬ ሲከተለው የነበረውን የፖለቲካ መስመር የሚለወጡ ይሆናል።
ብአዴን በክልል አወቃቀር፣ በሰንደቃላማ፣ በህገመንግስት ማሻሻል፣ ከአማራ ክልል ውጭ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መብቶች ዙሪያ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው በስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ስለሚሳተፉ ነባር የፖለቲካ አመራሮች እና በሌሎችም ፖለቲካዊ ጉዳዮች መሰረታዊ የተባሉ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ታውቋል።
የድርጅቱን አርማም በተመለከተ ብአዴን ለውጥ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ብአዴን በድርጅት የሚይዘው አቋም በኢህአዴግ ደረጃ በማቅረብ ተቀባይነት እንዲያገኝ እንደሚሰራ ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
No comments