መረጃ፣ ጥንቃቄ በደቡብ አፍሪካ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን (በልኡል አለሜ)
በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎች በሸቀጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ከትላንት ጀምሮ ንብረታቸው በገሀድ እየተዘረፈ ነው።
ወትሮውንም እንዲህ አይነቱን ተግባር ልምድ ያደረጉት ደቡብ አፍሪካዎች አሁን ምክንያት አላቸው “የሶማሌ፣ ፓኪስታን እና ኢትዮጵያውያን ዜጎች በሱቆቻቸው ውስጥ ጊዜ ያለፈባቸው የምግብ አቅርቦቶችን በመሸጥ ለልጆቻችን ሞት ምክንያት ሆነዋል” እያሉ ነው።
ጉዳዩ አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ የደቡብ አፍሪካ መንግስት እራሱን የቻለ መርማሪ ግብረሃይል አዋቅሮ ፍተሻ እያካሄደ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
ጊዜ ያለፈባቸው ብስኩቶች፣ ይህፃናት ምግቦች በአሰሳው በብዛት ተገኝተዋል። በተለይም ተመሳስሎ የተሰራ (fake) የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ እና የልጆች ዳይፐር (diaper) በሸማቹ ኅብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሱ ተነግሯል።
ይህን አጋጣሚ መሰረት ባደረገ መልኩ በተለይም በገጠሩ አካባቢ በሸቀጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን በዝርፊያው ተጎጂ ሆነዋል።
በደቡብ አፍሪካ በሸቀጥ ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል።

No comments