"የአማራውን ሚዲያ የሚቆጣጠረው ወያኔ ገና አልወደቀም" ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
"የአማራ ቴሌቪዥን ሲጋብዘኝ የተናገርኩትን እንደሚያስተላልፍ ተስማምተን ነው። የአማራ ድሃ ገበሬ ከሚከፍለው ግብር የአውሮፕላን ትኬት ተቆርጦልኝ፣ ሆቴል ተይዞልኝ ነው ወደ ባህርዳር የሄድኩት።
ያደረኩት ቃለ መጠይቅ 87 ደቂቃ ነበር። የተላለፈው ግን 31 ብቻ ነው። ከተናገርኩት ሩቡ ነው ማለት ነው። እንዲህ አይነት የሚዲያ አፈና በጣም አሳፋሪ ነው። ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም የባሰ ሆኗል ማለት ነው።
እኔ የተናገርኩትን ያስተላልፋታል የሚል ተስፋ ስለነበረኝ ነው ግብዧውን የተቀበልኩት። ላያስተላልፉት ለምን ይጋብዙናል? የአማራን ሚዲያ የሚቆጣጠረው ወያኔ ገና አልወደቀም።
በዚህ ሁኔታ ስለ ትግል እንጅ ስለ ለውጥ ማሰብ አይቻልም። በጣም በጣም አዝኛለሁ"
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበት ሁኔታ ስለ ጉዳዩ በፅሑፍ ለመግለፅ የማያመች እንደሆነና በቅርቡ በፅሁፍ ሊያሳውቅ እንደሚችል በስልክ ገልፆልኛል።
No comments