Latest

አሁን የደረሰን ዜና



በራያ ዋጃ ጥሙጋ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት በተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፖሊስ ጥይት መተኮሱ ተገለፀ::

ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መቁሰላቸው ታውቋል:: የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፎቶግራፍና ኮከብ የሌለበትን ሰንደቅዓላማ በሰልፉ ላይ በመታየቱ የተበሳጩት የአከባቢው የመንግስት ባለስልጣናት ታጣቂዎችን በማሰማራት ህዝቡን ለመበተን ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም::
 

የህዝቡ ሃይል ሲጠነክር ታጣቂዎቹ ማፈግፈጋቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: 

ዋናው የትራንስፖርት መስመር የተዘጋ ሲሆን ከአላማጣ ወደጥሙጋና ዋጃ ማለፍ እንደማይቻል ከስፍራው ከተላከልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል::

No comments