ሴራው ሲጋለጥ! ፈንጅ እንደሚፈነዳ ትህነግ/ህወሓት ትናንት ቀድሞ ፅፎታል! የለሁበትምን ምን አመጣው? (ጌታቸው ሽፈራው)
ፈንጅ እንደሚፈነዳ ትህነግ/ህወሓት ትናንት ቀድሞ ፅፎታል! የለሁበትምን ምን አመጣው? (ከስር ያለው የጥቃቱ ቅድመ ዝግጅትን የሚያሳይ ፅሁፍ ነው። ይህ ፅሁፍ የትህነግ/ህወሓት አመራሮች “ጥያቄ ኣለኝ ጓዶች በሚል የሚፅፉበት ገፅ ላይ ትናንት የወጣ ፅሁፍ ነው። አንድ አራት አይና ጓደኛዬ ጠቁሞኝ አየሁት። ለጥቃቱ ዝግጅት የተፃፈ ነው። ህወሓት የለበትም ተብሎ ትናንት የተፃፈ። አንብቡት)
የስጋት መግለጫ Worst Case Scenario Analysis (ጥያቄ ኣለኝ ጓዶች ገፅ ለይ)
ኢሳያስ ሁሌም አንድ ምኞት አለችው። የተበታተነች ኢትዮጵያ ማየት። የለማች ኤርትራ አንድም ቀን አልሞ አያዉቅም። ምቀኝነት የፖለቲካ ንድፈ ሃሳብ የሆነባት ሃገር ናት። ኢሳያስ የሰልፉን ጥሪ ተከትሎ ለምን ምላሽ ሰጠ ብሎ የጠየቀ አላየሁም። መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ነው። ጥሪዉን ተቀብያለሁ ባለበት መግለጫ “ጥሪዉን የተቀበልኩት ህወሓት ስላበቃላት ነው” ይላል። ይህ አደገኛ መርዝ ነው።
ሻዕብያ ከየትኛዉም ሃገር ጋር ያለው ግንኙነት በቁማርና ለማታለል በሚፈልግ ሴራ ነው። በኢሳያስ አገላለፅ ሽጣራን ደወራን ይለዋል፤ ኦፊሽያሊ። የሰሞኑ የሻዕብያ ጨዋታም ሰልፉን ተከትሎ የመጣ ሽጣራ ሊሆን ይችላል። ሰዎቹ ማፍያዎች ናቸው፤ መዘናጋት እንዳይኖር። ጠንቅቆ ያዉቀኛል ብለው የሚያስቡት ጌታቸው አሰፋ አለመኖሩም ሌላ ስሌት ዉስጥ ሊከታቸው ይችላል።
ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል። ይህ ግን ነገሮች ባሰብነው እና ባቀድነው መንገድ ብቻ ይሄዳል ማለት አይደለም። ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ያነገቡት አላማ ዕርቅ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ መቻቻል፣ መከባበር እና አንድነት ቢሆንም በሚገርም ሁኔታ አንዳንድ የጠቅላዩን መንፈስ እንኳን ሊገባቸው ልባቸው በጥላቻ፣ በቂም በቀልነት የተሞላ የግልና የህዝቦች መብቶች ለመደፍጠጥ ያሰፈሰፉ ጭምር መሳተፋቸው አይቀርም። ጠቅላዩ ይህ ባይፈልጉትም የሚቀር ነገር አይሆንም። አብዛኛው የበጎ መንፈሱ ተጋሪ ቢሆንም ቅሉ። መአት የዉስጥም የዉጭም ሃይል ይኖራል፣ ይህን በጎ ነገር ወደ ክፉ መመስመር መቀየር የሚፈልግ። ከነዚህ ሁሉ ሃይሎች ቀዳሚው ተዋናይ ሻዕብያ ነው።
ሻዕብያ የሆነ የሽብር ጥቃት ቢፈፅም ምን ተብሎ እንደሚተረጎም ግልፅ ነው። ህወሓት ጥያቄ ስላላት ቦምብ አፈነዳች መባሉ አይቀርም። ሻዕብያ ደግሞ እንዳይጠረጠር የሰላም ጥሪዉን እንደተቀበለና ፀቡ ከህወሓት ጋር መሆኑ ተናግሯል። የሻዕብያን ባህሪ ጠንቅቀን ለምናዉቅ ሰዎች ይሄ ጨዋታ ከባድ ቁማር መሆኑ ይገባናል። ኢትዮጵያን ሲወር ግዜ መከላከያ ሚኒስቴሩና ደህንነት ሃላፊው አዲስ አበባ ነበር፣ ራሱ ኢሳያስ ዓረብ ሃገር ነበር። ከየመንም ከሱዳንም ከጁቡቲም ሲጣላ አዘናግቶ ነው።

አሁንም ሰልፉን በመበጥበጥ ጉዳት ካደረሰ እነ እንትና መባሉ ስለማይቀር አምባገነኑ ሻዕብያ የዶክተር አብይ ዴሞክራቲክ አካሄድ ጥሞት የሰላም ጥሪ የተቀበለ አይመስለኝም። ኢትዮጵያን ለመበተን ደግሞ ታላላቅ በጎ ድግሶች ወደ ሁከት አዉድማ መቀየር ነው።
መንግስት ከፈተኛ ጥንቃቄ ያድርግ። ሻዕብያ ሰላምም ልማትም የሚፈልግ መሪ አይደለም። ኢህአዴግን ለማፍረስ ኮር ሃይል መምታት የሚል ፍልስፍናው ከህወሓት ጋር ዝንተ አለሙ ፀብ ዉስጥ ከቶታል።ተደጋጋሚ ሽንፈት ስላስጎነጨው ሻዕብያ ከህወሓት አልፎ የትግራይ ህዝብን የሚጠላ ሰይጣን ነው። የሰልፉ አዘጋጆች፣ የፀጥታ አካላት፣ ተሳታፊዎች ከባድ ጥንቃቄ እና ዝግጁነት ማድረግ አለብን።

ነገ የሆነ አደጋ ተፍጥሮ ወደ መረጋገጥ እና ፍረጃ ከተገባ የነገው ሰልፍ የመጨረሻችን መጀመርያ ይሆናል። ህዝብና ፓርቲ ለይቶ በማያይ እና ለይቶ ለማየት ፍላጎት በሌለው ህዝብ ዉስጥ ዳፋው ማን ጋር እንደሚላከከ ይታወቃል። መተላለቅ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ይደረግ። እምነቴና ፀሎቴ የነገው ሰልፍ ጠቅላያችንን ከጎንህ ነን የምንልበት እንዲሆን ብቻ ነው። አንዱን ቆርጦ አንዱን የሚስም ሻሞላ የለምና ሁላችንም ጠላቶች ሊያደርሱብን ከሚችሉ ጥፋቶች ሃገራችንን እንከላከል።
I Hope For The Best, But I Also Prepare For The Worst!

No comments