Latest

በቃ !! በተለይ አማራዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በቃ!! (አሌክስ አብርሃም)


ይሄ ህዝብ የራሱን ልጆች ረሃብና በሸታ እየፈጃቸው የመላው ኢትዮጲያዊያንን ልጆች ከባእድ ሲታደግ የኖረ ህዝብ ነው! ውለታው ይሄ ነው ?አገር እንደሌለው ከመሬት እንዳበቀለ ሙጃ በገጀራ መጨፍጭፍ ነው ምላሹ? የማንም ዘረኛና የጥላቻ ልጆች እጅ መሞከሪያ ነው? ይሄ ነው በቃ ? ስንቱን ነብሰ በላ <<ቀስ በቀስ ማሰተማር ነው >> በሚል ብሂል እንደአዲስ ለሚወለድ ግልፈተኛ ሁሉ ፍቅር እንዲማር የአማራው ነብስ ፊዳ መሆን አለበት?
  • ይሄ ህዝብ አገሩን እንደማተቡ አንገቱ ላይ አስሮ ለዚች አገር በየጢሻው አልወደቀም ? 
  • ነብሱን አልሰጠም? ውለታው የልጆቹን ነብስ በጭካኔ መንጠቅ ነው? 
  • ቤተ ክርስቲያን እንደገባ ውሻ ማካለብ ነው ? 
  • ይሄ ህዝብ ቤቱ ከነቤተሰቡ በላዩ ላይ እየተቃጠለ ቤተ እምነታችሁን ነብሱን ሰጥቶ አላቆየላችሁም?
  • በራሱ ክልል እንኳን ተመችቶት መኖር ያልቻለ ህዝብ በየሄደበት የማንም የጥላቻ አፍ መፍቻ ! ምንድነው ? 
ከምር ምንድን ነው? እንደህዝብ የበደለው ምንድን ነው?በዚህ ሶስት ወር እንኳን ከስንት ቦታ ተገፋ ሰንት ልጆቹን ሰዋ? አገሪቱ ከዳር እስከዳር መርዝ ተዘርቶባት እከሌን ከከሌ ሳትለይ መራዥ ለጆች እያፈራች ነው ግን አማራው ላይ በዛ !!

No comments