አርበኞች ግንቦት 7 በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ታጣቂዎቹ የትጥቅ ትግላቸውን እንዲገቱ ትዕዛዝ አስተላለፈ
የትንሳኤ ራዲዮ በዛሬው ጥንቅር
- አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የአመጽ ትግሉን መግታቱን አስመስልክቶ ዛሬ ባወጣው ልዩ መግለጫ ዙሪያ ከድርጅቱ የሕዝብ ግንኙንት ኃላፊ ከአቶ አበበ ቦጋለ ጋር ቆይታ አድርገናል።
- በነገው የአዲስ አበባ ሰልፍ ዶክተር አብይ ይገኛሉ።
- ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማመስግርን እና ጅምር የለውጥ እርምጃቸውን ለማበረታታት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የተጠራው የነገው ታላቅ ሰልፍ ሕብረ ብሔራዊነትን ባከበረ እና አንድነትን ባንጸባረቀ መልኩ በስኬት እንደሚካሄድ ከአስተባባሪዎቹ አንዱ አክቲቪስት ስንታዪሁ ቸኮል ለትንሳኤ ገልጿል።
- በናዝሬት ሕዝቡ እስከ ነገ አንጠብቅም በማለቱ፣ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የከተማዋ ጎዳናዎች በመኪና ጡሩምባ እና በዕልልታ ደምቀዋል።
- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ንግግራቸው “ ሕወሓት ማለት የትግራይ ሕዝብ ማለት አይደለም” ብለው መናገራቸው ያበሳጫቸው አንጋፋ የድርጅቱ መሪዎች በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ ሕዝቡን “ሕወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ነው!” የሚል መፈክር አስይዘው- ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሚቃወም መልኩ መልኩ ሰልፍ ማስወጣታቸው፣ ጥቂት የማይባሉ የትግራይ ተወላጆችን ቅር አሰኝቷል።
- በቅጽል ስማቸው “ጆቤ” የሚባሉት የቀድሞው የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጄር ጄነራል አበበ ተክለሀይማኖት መቀሌ የመሸጉትን ሽማግሌዎቹን የሕወሓት ሰዎች አትስሟቸው። እነሱን ያስጨነቃቸው የራሳቸው ማዕረግና ሥልጣን እንጂ የትግራይ ሕዝብ ጭግር አይደለም ሲሉ ለሕዝቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ትንሳኤ- የእርስዎ ራዲዮ!
No comments