Latest

በአውስትራሊያ ለምትኖሩ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች፣ አክቲቪስቶችና ሃገር ወዳዶች በሙሉ

በአውስትራሊያ ለምትኖሩ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ በተለይም በአማራ፣ በጉራጌ፣ በስልጤ፣ በጋሞ፣ በዶርዜ፣ ወዘተ ማህበረሰቦቻችን ላይ ማንነታቸዉን መሰረት ያደረቀ ጥቃት እንዲፈፀም ቅስቀሳ እያደረገ ወንጀሉን እያቀጣጠለዉ የሚገኘዉ ፀጋየ አራርሳ የተባለዉ ሰዉ የሚኖረዉ አዉስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ ነዉ::

ጸጋየ አራርሳ በአደባባይና በግልፅ በማን አለብኝነት ወንጀሉን እያስተባበረ እያስፈፀመ በአዉስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ በሰላም እየኖረ ነዉ::

አዉስትራሊያ የሰዉ ልጆች ሁሉ መብት የሚከበሩባት ሰላማዊ አገር እንጅ ተደብቀዉ ወንጀል እየቀፈቀፉ የሚያስፈጽሙባት አገር አይደለችም::

የአዉስትራሊያ ሕግም አንድ ሰዉ አዉስትራሊያ ተቀምጦ ውጭ አገር ወንጀል እንዲፈጸም እያቀነባበረ (ያዉም በሰዉ ዘር ላይ በማንነቱ ምክንያት በጅምላ ጥቃትና ጭፍጨፋ የመፈፀም ወንጀል) እያቀነባበረ በሰላም እንዲኖር አይፈቅድም::

ስለዚህ ከአዉስትራሊያ የሰብዓዊ መብት የሕግ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ሕጋዊ እርምጃ መዉሰድ እንድንችል ለመመካከር በአውስትራሊያ የምትኖሩ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች በሙሉ በዉስጥ መስመር አግኙኝ እና ተገናኝተን በጋራ ስለምንወስደዉ ሕጋዊ እርምጃ እንመካከር::

በማንኛዉም የሰዉ ልጅ ላይ በማንነቱ ምክንያት የሚፈፀም ወንጀል ያሳስበኛል የሚል ሁሉ በጋራ እንንቀሳቀስ:: ዛሬ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉ ወንጀል ነገ በእኛ ላይ መደገሙ አይቀርምና ቸል አንበል::

አንተነህ ሙሉጌታ
የሕግ ባለሙያ

No comments