Latest

የሀዘን መግለጫ (ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ - አብን)

የሀዘን መግለጫ (ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ - አብን)

በሰሜን ወሎ ዞን በሀብሩ ወረዳ ዉስጥ ባለዉ ህዝባችን ላይ በተቀነባበረ መልኩ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እንደተጋረጠ አሳዉቀን የነበረ መሆኑ ይታወሳል። 


በተለይ በወረዳዉ ዉስጥ ያሉት የአብን አባላት ላይ ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት እየደረሰባቸዉ መገኘቱን ገልፀናል። ቀደም ሲል የአብን የሀብሩ ወረዳ ሰብሳቢ ላይ ሊፈፀም የነበረዉ ጥቃት የከሸፈዉ በአካባቢዉ ህዝብ መከላከል መሆኑንም ገልፀናል።  

በአካባቢዉ ህዝብ ላይ እየተፈጠረ ያለዉን ችግር የክልሉና የፌዴራል መንግስቱ ተገንዝበዉ መፍትሄ እንዲሰጡ በማለትም በመግለጫችን መጠየቃችን ይታወሳል። ነገር ግን ያቀረብነዉ ጥያቄና መግለጫ ሰሚ በማጣቱ የወረዳዉ ህዝብ ለተጨማሪና አጠቃላይ ጥቃትና አለመረጋጋት እንዲጋለጥ ሆኗል።  

ትላንት የራያ ቆቦ የአማራ ልጆችን ከህወሀት ሰዎች ጋር ሆኖ ችግር ሲፈጥርባቸዉ የነበረዉ ሲሳይ ገዙ የተባለ ግለሰብ አሁን የሀብሩ ወረዳ ደህንነት ነኝ የሚል እና የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደሪ የሆነዉ ያረጋል ኃይሉ የተባለ ግለሰብ ዋጃ አካባቢ ከሰፈረዉና በሀብሩ ወረዳ ከገነባዉ ጊዜያዊ 

ካምፕ የመከላከያ ሀይል በልዩ ሁኔታ ትግርኛ ተናጋሪዎች የሆኑ ብቻ ጋር ቡድን ፈጥረዉ በመሰማራት ከተልእኳቸዉ ዉጭ በሆነ ተግባር በመቀናጀት "አብን ህገወጥና የሽብር ድርጅት ነዉ" በማለት ባደባባይ እየለፈፉ አባላቶቻችንን ሁሉ ከቤታቸዉ ወጥተዉ ጫካ ዉስጥ ዉለዉ እንዲያድሩ አድርገዋቸዋል። 

በዛሬዉ እለት ደግሞ የወረዳዉ የአብን አባል የሆነዉን ወንድማችን ያሲን አሊ ያሲንን በጥይት ተኩሰዉ በመምታት ገድለዉታል።  

ግድያዉን ደግሞ በተቀናበረ ሴራ እነሱ እንዳልፈፀሙት በማስመሰል የአካባቢዉን ህዝብ እርስበርስ ለማጋጨት ሞክረዉ ሳይሳካላቸዉ ቀርቷል። 

የወንድማችን ያሲን የቀብር ስነስርአት ተወልዶ ባደገበት፣ ቤተዘመዶቹ ባሉበት ዛሬ ቀን ላይ ተፈፅሟል። ይህ ግድያ አልበቃ ብሎ የሀብሩ ወረዳ የአብን ሰብሳቢ የሆነዉን ሌላ ወንድማችንን ለማፈን እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የአካባቢዉ ህዝብ በማወቁ በድጋሜ ያልተሳካላቸዉ ሆኖ ነገ እነሙሉቀን ተስፋዉን እና የልሳነአማራ ልጆችን ለመቀበል ወልድያ ከተማ ይመጣል በሚል እየጠበቁት መሆኑን ተረድቶ በዚሁ ምክንያት እንደማይገኝ ገልፆልናል።

ስለሆነም:-

1/ ለወንድማችን ያሲን መሀመድ ያሲን ነፍስ ይማር እያልን ለወላጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላዉ የአብን ቤተሰብ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን። በቀጣይም አብን ከጎናቸዉ እንደሚቆም ለማረጋገጥ እንወዳለን።  

2/ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በአካባቢዉ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉን ጥቃት በማዉገዝ መንግስት ተገቢዉን እርምጃ እንዲዎስድ ቀድመን ባሳሰብነዉ መሰረት ባለመፈፀሙ ተጨማሪ የፀጥታ ስጋት እንዲፈጠርና ወንድማችን ህይወቱን እንዲያጣ ሆኗል፣

3/ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) በወንድማችንና በአባላችን ላይ የደረሰዉን የሞት አደጋ በተመለከተ ተገቢዉን ሕግ በመጠቀም ገዳዬቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደምንሰራ እየገለፅን አሁንም ቢሆን በተቀናጀ መልኩ በህዝባችንና በአባላቶቻችን ላይ እየደረሱ ያሉት ጥቃቶች እንዲቆሙና እስካሁን ለተፈፀሙት ጥቃቶች ኃላፊ የሆኑት ላይ መንግስት ርምጃ እንዲዎስድ በድጋሜ እያሳሰብን


ይህ ባስቸኳይ የማይፈፀም ከሆነ ግን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) አባላቶቻችንና መላዉ የአማራ ህዝብ ራስን የመከላከልና እንዳግባብነቱ በሂደት የሚወሰኑ አግባብበት ያላቸዉን ርምጃዎች ህዝባችን እንዲወስድ ይፋዊ ጥሪ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን።
 

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

No comments