Latest

Getish Mamo Tekebel 4 (ተቀበል አራት) - New Ethiopian Music 2018 (Official Video)

Getish Mamo Tekebel 4

Ethiopian Music : Getish Mamo ጌትሽ ማሞ Tekebel 4 (ተቀበል አራት) - New Ethiopian Music 2018(Official Video)



መጣ መጣ ያ ቀን
በቃል በቃል በቃል ሀገር ሲድን

ለካ ያጣነው ፍቅር ነበር
እንደሰው እንዳገር የጎደለን ነገር

እኛ ያጣነው ይሄን ነበር
እንደሰው እንዳገር የጎደለን ነገር

ሸርሽሮ ሸርሽሮ ነገር አንጀቴን
ሊቆርጠው ነበረ ርቆኝ ይሄ ቀን

እስቲ ላወድሰው ላወዳድሰዉ
ከነሙሉ ክብሯ ስሟን ለጠራዉ
ይሄን ጀግና እስቲ ልጥራዉ
ቄሮ...ፋኖ...ዘርማ አንተ ያገር አርማ

ከፍ አለ ሰንደቁ ደስታውም ታየኝ
ድሮም ባገሩ ነው ሚለካው ታማኝ

እናቱ ሲወልዱት አሉት አንዳርጋቸው
ማን ያውቃል የዛሬ ቀድሞ እንደታያቸው
ባንዷለም በእስክንድር እውነትን ፍለጋ
ጨልሞ አልቀረም ና ብርሃኑ ነጋ
ና ... ና ...ና ...ና ...ና... ና

ደመቀ ሃገሩ ገዱ ቢቀናቸው
የለማ ሆነና አብይ ጉዳያቸው

እንዴት ነው ወገኔ እንዴት ነው ኤርትራ
ገዛ አባ ሻወል እንዴት ነው አስመራ
የከረመ ፍቅር አለ ከኔ ጋራ

Lyrics & Melody: Getish Mamo (ጌትሽ ማሞ)
Arrangement: Wondimeneh Assefa /Riga Recording Studio (ወንድሜነህ አሰፋ)
Masinqo: Degsew Abebe (ደግሰው አበበ)
Director: Seifu Bekele

No comments