Latest

የአባቴን ነገር አለማወቅ ነው!!!!

እምዬ ምኒልክ

ይህ የአዲስ አበባ እምብርት ፣ የእምዬ ምኒሊክ ሃውልት አምባ ነው!

  • የአክሱምን ከተማም ሆነ ፣ የአክሱማውያንን ርቀት የምትለካው ከዚህ ስፍራ ዜሮ ብለህ ጀምረህ ነው!
  • የላሊበላንና የጎንደርን ርቀት የምትመትረው ከዚሁ ከፒያሳ የእምዬ ሃውልት ስር ተነስተህ ነው!
  • የጣሊያንን ጦር የመቅኔ ቋቱን የሰበሩበት ፣ የሶሎዳ ተራሮች ሰንሰለት አድዋ አባቶቼ ጉዟቸውን የቀደሱት ከዚሁ ነው!
  • በጭቆና ቀንበር ስር ሲሰቃይ የኖረው የጥቁር ዘር በሙሉ እውነተኛ የብርሃን ውጋጋን አይቶ፣ ነፃነቱን ያወጀበት እለት የሚጀምረው ከዚሁ ሀውልት ስር ነው! 
  • የሶስት ሺህ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ፣ ላይለያይ ተጋምዶ ፣ ተፈትሎ እና ተውቦ ውሉ ከነጥለቱ የተሰፋው ፣ በእምዬ ምኒሊክ ሃወልት ስር ነው!
  • ይህ በጳጳስ ጀግናው ፣ እንኳን ኢትዮጵያን ምድሪቷን በጣሊያን ላይ የገዘቱትን ኢትዮጵያዊ ፣ አቡነ ጴጥሮስ ከጊዮርጊስ ቁልቁል በስስት እያየ ፣ የንጋትን ፀሐይ ፣ የሌትን ድቅድቅ በግርማ የሚያሳልፍ ፈርጥ ፣ የልቤ ገሚሱ ነው!
እኛ ኢትዮጵያኖች ስናየው በደስታ አይናችን በእምባ ይሞላል፣ በኩራት ልባችን ይነፋል፣ እለት እለት ውስጣችን የንጉሱን ገድል ያወድሳል!

ስለዚህ ይህ ሃውልት ብቻ ነው ብለህ ያሰብክ ካለህ፣ ላስተምርህ ፈቃዴ ነው! 

  • ይህ ማህተቤ ነው! 
  • ይህ የምስጋና ምኩራቤ ነው! 
  • ይህ የአያት የቅድመ አያቴ ፣ የአባቴ ፣ ለኔም የማንነቴ ፣ ለልጆቼ እና ለልጅ ልጆቼ የማንነታችን መሰረት ነው!

No comments